‘የጉዳት ሰለባ ለሆኑ ኢትዮጵያውን መብት መቆም አልቻለም’ ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች የአውሮፓ ህብረትን ተቸ

https://gdb.voanews.com/9D771801-CC21-4318-B3E9-1B458CE3D4DB_w800_h450.jpg

ሂውማን ራይትስ ዎች ትላንት ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ህብረት እና አባላቱ ጄኔቫ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክር ቤት፡ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ሁኔታ አስመልክቶ ለሚያደርገው ዓለም አቀፍ ክትትል ከሚሰጡት ድጋፍ አፈግፍገዋ፡ ሲል ነው የተቸው።

የሚቀጥለው አርብ ጥቅምት 2, 2016 የሚጠናቀቀውን የመንግስታቱን ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክር ቤት ጉባኤ አስመልክቶ አገራት የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ እስከ ትላንት ሰኞ ጥቅምት 23, 2016 ድረስ ጊዜ እንደነበራቸው ተመልክቷል።

በምክር ቤቱ በታዘዘው መሰረት የኢትዮጵያን የሰብአዊ አያያዝ የሚከታተለው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች ቡድን በበኩሉ፡ ከትላንት በስቲያ ሰኞ የቅርብ ጊዜውን የጥናት ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት “ለጭካኔ ወንጀሎች ስጋት ደቃኝ የሆኑ ምክንያቶች ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ” ሲል ደምድሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply