
“የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል!” ዳዊት አስራደ በዛብህ በመማሪያ መጻህፍት መዛባት ላይ አስቀድሞ ብዙ ንትርክ ውስጥ የተገባበት ስለነበር አብዛኛው ሰው የሚያውቀው ነው። የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጥላቻ በአዲስ አበባችን በ3ኛ ክፍል የክንውን እይታ በተባለው ትምህርት አሰጣት እንዴት እንድሚገለጽ በልጀ ባርኮት ፈተና ላይ አየሁት። ልጆቻችን ኦሮምኛን በግድ እንዲማሩ ያደረገው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መጽሀፉ በኦሮሞ ብልጽግና እንዲነገሩ እና እንዲሰርጹ የሚፈለጉ ነገሮችን ብቻ ያካተተ ከመሆኑ በላይ በትምህርት አሰጣጥ የሚገለጹ ነገሮችም እንዳሉ ዛሬ ተምሬ መጣሁ። “በኢትዮጵያ ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ የኖሩ ነዋሪዎች ምን በመባል ይታወቃሉ ተብሎ ለቀረበለት የፈተና ጥያቄ “ኢትዮጵያዊ” ብሎ በመመለሱ ማርክ ተቀነሰበት። ዛሬ መምህርቱን ሂጄ “ታዲያ ምን በመባል ነው የሚታወቁት ብየ ጠየቅሁ።” እናም “ጎሳወች እና ነገዶች” ነው የሚባሉት ብለውኝ አረፉ። “መጻህፉ ላይ እኮ በግልጽ እንዲህ ተብሎ አልተጻፈም!?” ስል ሀይለቃላዊ ጥያቄ አቀረብኩ። “አስተምሩ እንደተባልነው ነው ያስተማርነው” አሉ መምህርቷ። እናም አብረን እናስተካክለዋለን ተባብለን ልጀ ልክ ስለመሆኑ ሊያስረዱት እና ውጤቱንም ሊያስተካክሉ ለክፍሉ ተማሪወችም ይህ ሊሆን መምህርቷ ቃል ገብተው ተለያየን።
Source: Link to the Post