የጉጂ አባ ገዳዎች 'ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው ሲሉ አወጁየጉጂ አባ ገዳዎች በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው ታጣቂው ቡድን 'ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው ሲሉ አወጁ። አባ…

የጉጂ አባ ገዳዎች ‘ሸኔ’ የኦሮሞ ጠላት ነው ሲሉ አወጁ

የጉጂ አባ ገዳዎች በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው ታጣቂው ቡድን ‘ሸኔ’ የኦሮሞ ጠላት ነው ሲሉ አወጁ።

አባገዳዎቹ መንግሥት ሸኔ የሚለው እና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው ቡድን ‘የኦሮሞ ጠላት ነው’ ሲሉ የፈረጁት በቡድኑ በርካታ ንጹሃን ዜጎች በመገደላቸው ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የቦረና አባ ገዳ የሆኑት ኩራ ጃርሶ ታጣቂ ቡድኑን በተመሳሳይ ‘የኦሮሞ ጠላት ነው’ በማለት አውጀው ነበር።

የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ባለፈው ዓመት ይህንን ታጣቂ ቡድን ‘ሸኔ’ን እና ህወሓትን አሸባሪ ድርጅቶች ሲል መፈረጁ ይታወሳል።

በቅርቡም እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለውና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን መንግሥትን ለመጣል ከህወሓት ጋር በትብብር እንደሚንቀሳቀስ ይፋ አድርጓል።

ባህላዊው መሪዎቹ፣ ታጣቂው ቡድን ላይ ውግዘት ያስተላለፉት “ኦሮሞ ሆኖ ኦሮሞን የሚገድል ጠላት ነው” በማለት እንደሆነ የጉጂ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በጉጂ ሕይወት እጅጉን ፈታኝ ሆኗል የሚሉት አባ ገዳ ጂሎ፤ “የኦሮሞ ነጻነት ጦር ለኦሮሞ ሕዝብ ነው የምታገለው ይላል። ለኦሮሞ የሚታገል ከሆነ ኦሮሞን መግደል የለበትም” ብለዋል።

በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ማለትም በጉጂ ዞን እና በምዕራብ ጉጂ ዞን ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ2000 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ይናገራሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

መስከረም 08 ቀን፣ 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply