የጋምቢያው ፕሬዚዳንት በድጋሚ ተመረጡ

https://gdb.voanews.com/19AED981-F6E0-4933-8F2A-CC1E2EE29556_w800_h450.jpg

የጋምቢያው ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ብሄራዊ ምርጫ 53 ከመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምጽ በማግኘት አሸናፊነታቸውን አረጋገጡ፡፡

የጋምቢያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው ውጤት አሸናፊ መሆናቸው የተረጋገጠው ፕሬዚዳንት ባሮ የተወዳደሩት ከአምስት እጩ ተፎካካሪዎች ጋር እንደነበር ተገልጿል፡፡ 

ከእርሳቸው ቀጥለው ሁለተኛ የወጡት የተባበሩት ዴሞክራቲክ ፓርቲው መሪ 28 ከመቶ ማግኘታቸውም ተመልክቷል፡፡

ትንሿ የምዕራብ አፍሪካ ሃገር ጋምቢያ ለ22 ዓመት የገዟትን የቀድሞ ፕሬዚዳንትዋን እኤአ በ2016 በተካሄደ ምርጫ ከሸኘች ወዲህ ይኸኛ የመጀመሪያው ምርጫ መሆኑ ተነግሯል፡፡ 

2.5 ሚሊዮን ከሚሆነው የሃገሪቱ ህዝብ ለመምረጥ የተመዘገበው ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ መሆኑን ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply