የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎታቸውን በተሻለ ጥራት እያከናወኑ ነው-ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎታቸውን በተሻለ ጥራት እያከናወኑ ነው-ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎታቸውን በተሻለ ጥራት እያከናወኑ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ከጋምቤለ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና ከሀይለማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን መስራች ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር በጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሚኒስትሯ የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ካደገ አንድ አመት ከስድስት ወር ገደማ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ በሆስፒታል ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥራት ደረጃ እያደገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሰረተ ልማት ደረጃም የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በእናቶች እና ህፃናት ጤና እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተሰሩ የማስፋፊያ ስራዎች አበረታች መሆኑን አንስተዋል።

በስነ ወሊድ እና በስነ ተዋልዶ ዙሪያም ሆስፒታሉ መሻሻል እንዳሳየ ጠቅሰው፤ ከክትትል ህክምና ጀምሮ ክትባትና ሌሎች አገልግሎቶች ጥራታቸው የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል።

በጉብኝታቸው በሆስፒታሉ እንደከፍተት ስለታዩ ጉዳዮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ማብራሪያ የሰጡት ዶክተር ሊያ እንደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልነቱ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ሊኖረው ይገባ ነበር ነው ያሉት።

ሆኖም ሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና እንደማይሰጥ የገለፁ ሲሆን ይህንን ለማስጀመር ቦታዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

ለዚህም የጤና ሚኒስቴር እና አጋር አካላት ለህክምናው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን አሟልተው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቀጣይ እንደሚሰራም ነው የተናገሩት።

የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታልን የጎበኙት ሚኒስትሯ ሆስፒታሉን ከአንድ ዓመት በፊት እንዳዩት በማንሳት አሁን የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በቀጣይ ቀናት እንደ ሀገር የሚጀመረውን የኮሮና ቫይረስን የመከላል እና የመቆጣጠር ንቅናቄ በጋምቤላ ክልልም እንዲተገበር ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከሩ ነው።

ከሀይለማሪያም እና ሮማን ፋንዴሽን ጋር በመተባበር የእናቶች ፣ ጨቅላ ህፃናት እና የህፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ለማሻሻል እና ተመጣጣኝ የጤና ልማት ለማረጋገጥ ሰፊ የንቅናቄ መድረክ በነገው ዕለት በክልሉ ይካሄዳል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎታቸውን በተሻለ ጥራት እያከናወኑ ነው-ዶ/ር ሊያ ታደሰ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply