የጋሞ ዞን ሴቶች በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም…

የጋሞ ዞን ሴቶች በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጋሞ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መመሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅርተ አብረሃም እንደገለፁት ከአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚሆን ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን ተናግረዋል። ድጋፉ የተሰበሰበው በዞኑ ካሉ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ፍቅርተ 80 ፍራሽ ፣ 31 ኩንታል የቤት ቁሳቁስ ፣ 42 አልጋ ልብሶች ፣ ሃያ አምስት ትራሶች ፣ ብርድ ልብሶች ፣ 21 ኩንታል አልባሳት ፣ ጫማዎች እና ሌሎች የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች ከህብረተሰቡ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡ ድጋፉን የጋሞ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ እና የጋሞ ዞን የሴቶች ሊግ በጋራ በመሆን ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ለክልሉ ሴቶች አደረጃጀቶች አስረክበዋል ሲል የዘገበው የቢሮው ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply