የጋሸና ጭፍጨፋ! ጋሸና ከተማ በኢትዮጵያ ሀይሎች ጥምረት ድል በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደገባ ህዳር 22/2014 ዓ.ም ህዝቡ ከህወሀት ወረራ ነጻ መውጣቱን ማክበር በነበረበት ቀን…

የጋሸና ጭፍጨፋ! ጋሸና ከተማ በኢትዮጵያ ሀይሎች ጥምረት ድል በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደገባ ህዳር 22/2014 ዓ.ም ህዝቡ ከህወሀት ወረራ ነጻ መውጣቱን ማክበር በነበረበት ቀን በሁሉም አቅጣጫ በጥልቅ ሀዘን የተሞሉ ብዙ ለቀስተኞችን ተመለከትኩ:: ቀብር ሲደረግበት ወደነበረው ጋሸና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከደረስኩበት ሰአት ጀምሮ እስከወጣውበት ከአርባ በላይ አስከሬን በተለያየሰአት ሲቀበር አስተዋልኩ:: የቤተክርስቲያን ቀሳውስቶችን እና ነዋሪወችን ባወራሁ ጊዜ የህወሀት አሸባሪ ቡድን እንደ ጭና እና ተለያዩ ቦታወች ሽንፈት ሲገጥመው ሽንፈቱን ንጹሀን የአካባቢውን ሰው እንደሚገድል በጋሸና ከተማም በተለይ መውጫው ላይ በሚገኝ ቀበሌ ከባድ በግፍ የተሞላ ግድያ ምንም ከሁኔታወች ጋር ግንኙነት በሌላቸው ሰወች በአንድ ክፍል ውስጥ ተደብቀው የነ…በሩ 16 ሰወችን ጨምሮ በአንድ ቀን ከስልሳ በላይ ንጹህንን ጨፍጭፈው እንደ ሸሹ አስረዱኝ:: ከሞት ከተረፉትም አንደበት ከተገደሉት ውስጥ አባቶች እናቶች ህጻናት እና አዛውንት እንሚገኙበት አስረድተውኛል:: በቦታው የነበረው ጥልቅ የሀዘን ስሜት በአካባቢው ባህል በተለያዩ አሳዛኝ ዜማ ሚስቶች ለባላቸው አባት ለልጁ በሚያወጡት በቃላት የማይገለጽ እኔም በህይወቴ የማልረሳው ሀዘን ነበር:: ምንጭ:_ አቤል ጋሻው ጋሸና /ሰሜን ወሎ

Source: Link to the Post

Leave a Reply