You are currently viewing የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረጎ ለነሐሴ 19/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ…

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረጎ ለነሐሴ 19/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረጎ ለነሐሴ 19/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሐምሌ 26 ቀን 2014 የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካቀረበው መቃወሚያ ጋር በማገናዘብ ብይን ስለመስጠቱ ተገልጧል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት የሚታይ ቢሆንም ይርጋ እንዴት መቆጠር አለበት የሚለውን ጉዳይ በወንጀል ህጉ መሠረት ስናየው ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት ነው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው። ፍርድ ቤቱ ክሱን ከቀረበው ማስረጃ አንጻር መርምሮ እንዲከላከል ወይም በነጻ ለመልቀቅ ለነሐሴ 19 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply