የጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነነ መኩሪያ ስርዓት ቀብር ተፈጸመ፡፡የአንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ስርአት ቀብር በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡አንጋፋው ጋዜጠኛ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/snOfG32heKEOtYFgFWb4jOJJLLAvODozaVGprMPgKfB6bbuHfsDuQbxDeY8q7Y_GLnOokpdnb1tJlftXBh4QoPqnZygFnrj23tPEamBCNgtYuj4U-PMDbbcTOVoj8Cty_AdHIYY5r9sEjyZd2YqZyyccazKSjY1cwayDeUMPSxFFvmOBgd4ShG2E_iu88UQUv5dPXp7iAjH3UAYSetROHzUP0gPtNUwbVSVbWrDI6V3tlwl3W3cu_Uh_RxVKdaozZTTrySR8j6DmVW5Sf6MgWWkeZlXkE5spv57fBUHwbTausKqvGTiBPP5IK0jvxGACZxUe3yOkJMdklvp7GgMYFw.jpg

የጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነነ መኩሪያ ስርዓት ቀብር ተፈጸመ፡፡

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ስርአት ቀብር በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ከቅርብ ወራቶች በፊት ከህመሙ ጋር በተያያዘ እግሩን ማጣቱ ቢሰማም ከህመሙ ጋር ትግል እያደረገ ባለበት ሰዓት ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
በ1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ፤ በኢትዮጵያ በእግር ኳስ ተጫዋችነት፣ በጋዜጠኝነት እና በመጻሕፍት ደራሲነት ይታወቃል።

ከ30 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኝነት ያሳለፈው ገነነ መኩሪያ፤ኢህአፓ እና ስፖርት፣መኩሪያ እና ፍትሃዊ የጠጅ ክፍፍል መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ገነነ መኩሪያ በአሻም ቲቪ ትኩረታቸውን በስፖርት እና በታሪክ ላይ ያደረጉ “የገነነ” እና “ጥቁር እንግዳ” የተሰኙ ፕሮግራሞችን ለዓመታት በአዘጋጅነት እና አቅራቢነት ሲሰራ መቆየቱም ይታወቃል።

ለእግር ኳስ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦም፤ በ2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተሰናዳው የካፍ ኮንግረስ ላይ የረጅም ዘመን አገልግሎት ሜዳይ ተበርክቶለታል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply