የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የትምህርት ደረጃ እና እውቀት የቀሰሙባቸው አካባቢዎች! ዝክረ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ 2ኛ አመት የእረፍት መታሰቢያ አማራ ሚዲያ ማዕከል ካዘጋጀው የህይወት ታሪካቸው የተገ…

የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የትምህርት ደረጃ እና እውቀት የቀሰሙባቸው አካባቢዎች! ዝክረ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ 2ኛ አመት የእረፍት መታሰቢያ አማራ ሚዲያ ማዕከል ካዘጋጀው የህይወት ታሪካቸው የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ደምስ በለጠ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ፣ጽኑ ፣ደግ፣ርህሩህ እንዲሁም ዘመድ እና ጓደኛ ወዳድ የሆኑት እውቅ ጋዜጠኛ፡ገጣሚ እና ጸሀፊ ነበሩ። በአዲስ አበባ ልደታ አካባቢ የተወለዱት ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እውቅት የቀሰሙትም:_ ሀ)በደሴ_ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ትምህርታቸውን የተከታተሉት ወደ ደሴ አቅንተው ከአያቶቻቸው ቤት ነበር፡፡ አያቶቻቸው መቶ አለቃ ትርፌ እና ወ/ሮ እልፍነሽ መንገሻ ልክ እንደ ልጃቸው እየተንከባከቡ በንጉስ ሚካኤል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እስከ 6ኛ ክፍል እንዲማሩ ረድተዋቸዋል፡፡ ለ)በአዲስ አበባ_ ከ6 ዓመት የደሴ ቆይታ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በሲዊዲን ሚሽነሪ ት/ቤት ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በቀድሞው የተፈሪ መኮንን ት/ቤት በአሁኑ እንጦጦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመማር እውቀትን ቀስመዋል፡፡ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ያላቸውን ከፍተኛ የማወቅ ፍላጎታቸውንና ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን ዝንባሌ ተጠቅመው የራሽያኛና የጣሊያንኛ ቋንቋዎችን አጥንተዋል፡፡ በተለይ በአዲሰ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው በራሽያ ኤግዚቢሽን የራሽያኛ ቋንቋን በመማር አቀለጥፈው መናገር ብቻ ሣይሆን ይጽፋሉ፣ይተረጉማሉ፡፡ እስከ አሁን ለሕትመት ባይበቃም የፑሽኪን መጽሀፍን ወደ አማርኛ ተርጉመዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ባስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት በሩሲያ መንግስት ነፃ የትምህርት እድልን አግኘተዋል፡፡ ገና በ19 ዓመታቸው በ1979 ዓ.ም ነበር ወደ ሩሲያ አቀንተው የሥነ -ጽሁፍ እውቀትን የቀሰሙት፡፡ እስከ አሁን ድረስ በሩሲያው ጎርኪ የስነ-ጽሁፍ ተቋም ሁለቱ ጥቁር ተማሪዎች ማለትም ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳና ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የእውቀት ማዕድ ተካፋይ በመሆን ተመርቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በጆርናሊዝም፣ሊትሬቸርና ክሬቲቭ ራይቲንግ በማስተርስ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን በሀገረ ሩሲያ ለትምህርት ብቻ ለ7 ዓመት ያህል ቆይተዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጋዜጠኛው በቆይታቸውም ከጎርኪ የሥነ ጽሁፍ ኢንስቲቲዩት ትምህርታቸው በተጨማሪ የሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በሚል ደርግን ጨምሮ ኢህአዲግ መራሹ መንግስትን አምባገነናዊ አካሄድ ለማንም አይጠቅምም በማለት በጽኑ የታገሉና አያሌ ፈተናዎችን ያለፉ ጀግና እንደነበሩ በብዙዎች ተመስክሮላቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply