You are currently viewing የጋዜጠኝነት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ክስ፣ እስር እና መሳደድ ሲገጥማቸው የቆዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እና ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ ከሀገር ወጥተዋል።…

የጋዜጠኝነት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ክስ፣ እስር እና መሳደድ ሲገጥማቸው የቆዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እና ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ ከሀገር ወጥተዋል።…

የጋዜጠኝነት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ክስ፣ እስር እና መሳደድ ሲገጥማቸው የቆዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እና ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ ከሀገር ወጥተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ክስ፣ እስር እና መሳደድ ሲገጥማቸው የቆዩት የኢትዮ 251 ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እና የዘ_አምሓራ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ አዲሱ ደርበ:_ 1) የአማራ ህዝብ የጀመረውን ስር ነቀል ስርዓታዊ ለውጥ እና ህልውናን የማስከበር ትግልን የበለጠ ለማጠናከር በማለም፤ የተደራጀ የትግል አጋርና ሠፊ ነፃ ቀጠና ለመፍጠር እንዲሁም፣ 2) አገዛዙ በሚዲያ፣ በጋዜጠኞች፣ በማህበረሰብ አንቂዎች፣ በምሁራንና በሌሎችም ወገኖች ላይ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ እየፈጸመው ያለውን አፈና፣ እስር እና መሳደድን በማጋለጥ ለህዝቡ በነጻነት በቂ እና ወቅታዊ መረጃ በማድረስ ረገድ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ሲሉ ከሀገር መውጣታቸውን አሚማ አረጋግጧል። ይህንን ውሳኔ ሲወስኑም ከሚመለከታቸው እና መሬት ላይ ወርደው በአማራ ህዝብ ትግል ላይ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ካሉ ቁልፍ የትግሉ መሪዎች ጋር በስፋት ከመከሩ እና ከተስማሙ በኋላ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። የኢትዮ 251 ሚዲያ መስራችና ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር በሽብር ወንጀል በሌሉበት ከተከሰሱት 27 የአማራ ታጋዮች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን በዛሬው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ አውታሮች ጋዜጠኞቹ ትግሉን በመተው እንደተሠደዱ የሚናፈሠው ወሬ ካለው እውነታና ከጉዟቸው አላማ የራቀ መሆኑን አሚማ አረጋግጧል። ከጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እና ከጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ በተጨማሪም:_ 1) ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው፣ 2) ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ፣ 3) ጋዜጠኛ ያዬሰው ሽመልስ፣ 4) ጋዜጠኛ አበበ ባዩ እና ሌሎችም በሚደርስባቸው እስር፣ እንግልትና ወከባ ምክንያት ሀገር ጥለው መሰደዳቸው ይታወቃል። ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው፣ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እና ሌሎችም ከጋዜጠኝነት ስራቸው ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በሚፈጸምባቸው እስር የተነሳ እየተሳደዱ እንደሚገኝ ግልጽ ነው። አሁን ላይ በግፍ ታስረው ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከልም እንደአብነት:_ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጽሃፊው ታዲዎስ ታንቱ፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply