የጋዜጠኞቹ አለመፈታት! ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ ፣ ጎበዜና አሳዬን አቃቤ ህግ “ይግባኝ ልጠይቅ እችላለሁ” ስላለኝ አለቃቸውም አለ! መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር…

የጋዜጠኞቹ አለመፈታት! ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ ፣ ጎበዜና አሳዬን አቃቤ ህግ “ይግባኝ ልጠይቅ እችላለሁ” ስላለኝ አለቃቸውም አለ! መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ የቆዩት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ አሳዬ ደርቤና ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ባሳለፍነው አርብ መስከረም 27/2015 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው በዋስ እንዲፈቱ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ20,000 ብር ዋስትና አሳዬ ደርቤና ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እያንዳንዳቸውን በ 10,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል። ነገር ግን አርብ ከሰዓት በኋላ የተወሰነውን የዋስትና መብት መነሻ በማድረግ የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች የዋስትና ክፍያውን ከፍለውና ማስፈቻ ይዘው ወደ እስር ቤት ቢያመሩም ሰዓት አልፏል በሚል ሳይፈቱ ቀርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቤተሰቦቻቸውና ጠበቆቻቸው ዛሬ መስከረም 30/2015 ዓ.ም ከማለዳው ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት ፍ/ቤቱ በወሰነው መሰረት የዋስትና ፎርማሊቲ አሟልተው ከእስር ማስፈቻ ትዕዛዝ ቢያስገቡም አቃቤ ህግ በውሳኔው ላይ “ይግባኝ ልጠይቅ እችላለሁ” ብሏል በሚል ፖሊስ አለቅም ማለቱን ሮሃ አረጋግጣለች፡፡በጉዳዩ ላይ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡ ዘገባው የሮሃ ሚዲያ ነው ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply