You are currently viewing የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድንና ጎበዜ ሲሳይን በቀጠሮ መሰረት ችሎት ሳያቀርብ ቀረ:: ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ…

የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድንና ጎበዜ ሲሳይን በቀጠሮ መሰረት ችሎት ሳያቀርብ ቀረ:: ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ…

የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድንና ጎበዜ ሲሳይን በቀጠሮ መሰረት ችሎት ሳያቀርብ ቀረ:: ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ ላይ ዓቃቤ ህግ እመሰርተዋለሁ ላለው ክስ የ4 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ለዛሬ መስከረም 20/2015 ቀጥሮ ነበር፡፡… ነገር ግን መርማሪ ፖሊስ በቀጠሮው መሰረት ዛሬ ጋዜጠኞቹን መዓዛ መሃመድንና ጎበዜ ሲሳይን ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ የጋዜጠኞቹ ጠበቆቹ በበኩላቸው “ፖሊስ ጋዜጠኞቹን አለማቅረቡ ክስ የመመስረት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ያሳያል” በሚል በዋስትና እንዲወጡ ችሎቱን መጠየቃቸውን ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ችሎቱ ጉዳዩን ለዛሬ ከሰዓት የቀጠረ ሲሆን፣ በከሰዓቱ ቀጠሮም ፖሊስ ጋዜጠኞቹን ለምን እንዳላቀረበ የፊታችን ሰኞ መስከረም 23/2014 ዓ.ም ቀርቦ እንዲያስረዳ አዟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ፍርድ ቤቱ ወስኗል። የአማራ ተወላጆች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብለህ ዘግበሃል፣ ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ፎቶ ልከሀል በሚል ተወንጅሎ በ እስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት ተወስኗል። ከዚህ በፊት በነበረው ችሎት በ5 ሽህ ብር ዋስትና እንዲወጣ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ሳይወጣ ቀርቷል። ከጠበቃው ሄኖክ አክሊሉ ጋር የቀረበው ዓባይ ዘውዱ ትናንት በነበረው ችሎት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ክርክር የተደረገ ሲሆን ዛሬ ለውሳኔ መቀጠሩ ይታወሳል። ረፋድ ላይ የነበረው ችሎት የዋስትና መበት ይጠበቅለት ሲል ወስኗል። በተመሳሳይ የማህበረሰብ አንቂው አሳዬ ደርቤ በዋስትና እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡ነገር ግን ይህ ዜና እስኪጠናቀር ድረስ አባይ ዘውዱም ሆነ አሳዬ ከእስር አልተፈቱም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ወቅት ፍትህ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሰረት ዐቃቤ ህግ የሃሰት ወሬን በመንዛት፤ በውጊያ ውስጥ የወገን ጦር አሰላልፍና ቦታን ለጠላት እና ለህዝብ በማሳወቅ በህግ የተከለከለ ድርጊትን የፈጸሙ ናቸው ሲል በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ፣ ጎበዜ ሲሳይ ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ሲል የገለጸው ጎበዜ ሲሳይ፤”ቲዊተር የሚባል የማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ Amhara Perspective ተብሎ የተከፈተ የቲዉትር ስፔስ አካዉንት ላይ በቀን ነሃሴ 26/2014 ቀርቦ ባደረገዉ ንግግር ጠቅላላ ህዝቡ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የማይደግፍ ይልቁንም ህወሃት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ የሚፈልግ እና የሚደግፍ እና ወጣቱ ከመንግስት ጎን መሰለፍ የማይፈልግ አድርጎ በማቅረብ ሰራዊቱ በአካባቢዉ ያለ ህዝብ አይደግፈኝም ብሎ እንዲያስብ በማነሳሳት በህዝብና እና በሰራዊቱ መካከል ያለዉን መልካም ግንኙነት የሚጎዳ እሳቤ እንዲኖር ሰርቷል” የሚል ነው፡፡፣ በተጨማሪም ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም “አሁን በተከፈተው ጦርነት ውስጥም ሕወሓትን ፊት ለፊት እየተዋጉ የሚገኙት የፋኖ መሪዎችን ምሬ ወዳጆን እና ደምሌ አራጋውን ለመግደል በተደጋጋሚ ከኋላ እየተተኮሰባቸው ህይዎታቸው ተርፏል። በዚህ ሁኔታ እንዴት መንግስትን ተማምኜ ጦርነት እገባለሁ የሚል ወጣትም አለ።” ብሏል እንዲሁም የጥምር ጦሩን አሰላለፍ ይፋ አውጥቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡ አቃቤ ህግ ሁለተኛተከሳሽ ያለው አሳዬ ደርቤ እና 3ኛ ተከሳሽ ያላት ጋዜጠኛ መዐዛ መሃመድ ላይ የቀረበባቸው ክስ ደግሞ በሮሃ ሚዲያ አማካኝነት ነሃሴ 19/2014 ዓ.ም ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የነበረዉን ጦርነት ማጠናቀቅ ይቻል ነበር፡፡ ችግሩ ምንድን ነዉ ለመሸነፍ ዝግጁ ያልሆነ ጠላት ስላጋጠመን ሳይሆን ፍላጎት የሌለዉ መንግስት ስለነበረን ነዉ፡፡ ህወሃት ሲዳከም እፎይታ ጊዜ እየሰጠ ወደ ደቡብ ጎንደር ሲያመራ አፈግፍጉ የሚል ትዕዛዝ እየሰጠ በሀብት የሚጠናከርበትን፣የህዝብ ስነልቦና የሚንኮታኮትበትን መንገድ ሲጠርግ ነበር፣ህዝቡ ተጠናክሮ ከደቡብ ጎንደር ሲያወጣዉ ደግሞ በዛዉ ግለት ከማስቀጠል አንፃር የእፎይታ ጊዜ እየሰጠ እንደገና ወደ ወሎ የሚሄዱበትን መንገድ ሲያመቻች ነበር፡፡ እና የወንበር ስጋት ሲሆኑ ቀጥቅጦ ያባርራቸዋል፤ከወንበሩ የሆነ ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሲሆኑ ትቷቸዉ ይመጣል ማለት ነዉ” ብሎ አሳዬ ደርቤ ተናግሯል የሚል ነው፡፡ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ደግሞ በምታስተዳድረዉ ሚዲያ ይህን የአሳዬ ደርቤን ንግግር አስተላልፋለች የሚል ክስ ቀርቦባታል፡፡ ይህው የዐቃቤ ሕግ ክስ ፍርድ ቤት ደርሶ የመዝገብ ቁጥር የያዘ መሆኑንና የፊታችን ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ክሱ ለተከሳሽ እና የችሎት ታዳሚ ተነቦ ክርክሩ የሚቀጥል ይሆናል ብሏል፡፡ © ሮሃ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply