የግል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በሰራተኞች ላይ ምሬት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

የግል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በሰራተኞች ላይ ምሬት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሃገሪቱ የሚገኙ ኤጀንሲዎች ለሃገሪቱ ጥቅምን ሳይሆን ኪሳራን ለደሃው ህዝብ የላብን ውጤት ሳይሆን ከልክ ላለፈ የጉልበት ብዝበዛንና የምሬት ምንጭ ሆነዋል ተብሏል። ሰራተኞቹም ለምን ይህ ጉዳይ ተዘነጋ? ፣በሃገሪቱ የሚገኙ ኤጀንሲዎች ለምን በመንግስት የሚወጡ ህጎችን አያከብሩም? ሲሉም ጥያቄ አቅርበዋል። እነዚህ ኤጀንሲዎች በሚያሳድሩት ተፅእኖ ሰራተኛው ከስራው ያለ አግባብ እየተሰናበተና ተገቢ ያልሆነ የገልበት ብዝበዛ እየደረሰበት በመሆኑ በአፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉም ጠይቀዋል። ደሃው የላብን ውጤት ሳይሆን በድካሙ እንባውን ሲዘራ ለምን ዝም ይባላል? ሲሉ ለኢትዮጲያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጥያቄዎችን አቅርበዋል። እንደ ሰራተኞቹ ገለፃ ኤጀንሲዎች ደንብ ሲጥሱና እንዳሻቸው በደሃው ጉልበት ሲጫወቱ እየታየ ዝም እንዴት ይባላል? አዋጅ ይወጣል ግን ሲከበርም ሆነ ተግባራዊ ሲደረግ አይተን አናውቅም ይሄ መዘናጋት ሊያበቃ ይገባል መብታችንም ይከበርልን ሲሉ ለኮንፌደሬሽኑ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የስራ ላይ ደህንነት፣የሙያ ላይ ደህንነትን የመሳስሉ ደንቦች እየተዘነጉ ሳለ ለጉዳዩ አንድም የተጠናከረ ምላሽ የሚስጥ የሚመለከተው የመንግስት ተቋም የለም መንግስት ካልሆነ ወይ ሰራተኛውን ወይም ደግሞ ኤጀንሲዎችን ይምረጥ ሲሉ ጠይቀዋል። የኮንፌደሬሽኑ ፕረዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው የኤጀንሲዎች ጉዳይ እርግጥ የሃገሪቱ ከፍተኛ እራስ ምታት ሆኖብናል ያሉ ሲሆን በኤጀንሲዎቹ እንዲፈፅሙ የወጣውን አዋጅ ለማስፈፀም የተለያዩ መመሪያዎች ተግባራዊ ቢደረጉም ተፈፃሚነቱ ላይ ቅሬታ ይነሳል ብለዋል። ይህንን ችግር ለመፍታትም በኤጀንሲዎቹ ላይ የሚደረገው ቀጥጥር ተጠንክሮ እንደሚቀጥል ምላሽ ሰተውበታል በተጨማሪም በአዋጅ የወጡ መመሪያዎችና ደንቦችም ተፈፃሚ መሆን እንዳለባቸው ለዚህም ከሰተኛው ጋር በቅርበት እንደሚስራ ተናግረዋል። ኢትዮ ኤፍ ኤም

Source: Link to the Post

Leave a Reply