የግል የህክምና መስጫ ተቋማት ለቃጠሎ ህክምና አገልግሎት ፍላጎት አልባ መሆናቸው ለዘርፉ ትልቅ ፈተና ነው ተባለ፡፡

በመንግስት ሆስፒታሎች ከሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ የግል የህክምና መስጫ ተቋማት የተለያዩ የህክምና ዘርፎች ላይ አገልግሎት በመስጠት ክፍተቶችን ይሞላሉ፡፡

የቃጠሎ ህክምና በባህሪው ውስብስብ እና ድንገተኛ ከመሆኑ አንፃር ለዘርፉ የሚገባው ትኩረት አልተሰጠውም፤ ተገቢው የቃጠሎ ህክምና አገልግሎት እየተሰጡ አይደለም ሲሉ በየካቲት 12 ሆስፒታል የቃጠሎ ህክምና ክፍል ሀላፊ ዶክተር አብይ ሀይሉ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

በመንግስት ሆስፒታሎች አልተሸፈኑም ያላቸውን ህክምና እና የህክምና መስጫ መሳሪያዎችን በከፍተኛ ዋጋ አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋማት የቃጠሎ ህክምና አዋጭ አይደለም በሚል ወደ ዘርፉ እንደማይቀላቀሉም ዶክተር አብይ አስታውቀዋል፡፡

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply