የግሪክ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚደግፍ አዋጅን አፀደቀ

የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርምጃውን በጥብቅ አውግዛለች

የግሪክ ፓርላማ ትናንት ሐሙስ ባካሄደው ጉባኤ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ጥንዶች እንዲጋቡ የሚፈቅደውን ረቂቅ ደግፎ ድምፅ ሰጥቷል።ይህም ግሪክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊ ያደረገች የመጀመሪያዋ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሀገር ያደርጋታል።

ሶስት የቀኝ ፅንፍ ፓርቲዎች እና የግሪክ ኮሚኒስት ፓርቲ ግን ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል።የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ኢሮኒሞስ በበኩላቸው ሕጉን በጥብቅ አውግዘዋል።

ረቂቅ ህጉ 300 መቀመጫዎች ባሉት የግሪክ ፓርላማ በ176 የህግ አውጭ ተወካዮች በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ ውጤቱን “ለሰብአዊ መብቶች ትልቅ ምዕራፍ” ብለውታል። ግሪክ የጋብቻን እኩልነት በህግ የደነገገች በአውሮፓ ህብረት 16ኛዋ ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል።

ያም ሆኖ ህጉ ግሪካውያንን ለሁለት የከፈለ ሆኗል፤ በፓርላማው ፊትለፊት ህጉን የሚቃወሙ አካላት ሃይማኖታዊ ምስሎችን ይዘው ሲፀልዩ የነበረ ሲሆን፤ ደጋፊዎች ደግሞ የቀስተ ደመና ባንዲራዎችን በደስታ ሲያውለበልቡ መታየታቸውን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል።
የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply