የግብርና ሚንስቴር በ70 ቢሊዮን ብር ወጪ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ መፈፀሙን አስታወቀ፡፡

በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ 19.4 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልጋት የግብርና ሚንስተር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው በግብርና ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ከበደ ላቀው፣ ግዢ ከተፈጸመው 19.4 ሚሊየን ኩንታል ውስጥ 8.5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ጅቡቲ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ሰፊውን እና ትልቁን የሀገራችንን ሽፋን የሚይዘው የመኸር ምርት በመሆኑ፣ 55 በመቶ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ለዚህ አገልግሎት እንደሚውልም ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት አጋጥሞ የነበረው የማዳበሪያ እጥረት እንዳያጋጥምም ቀድሞ የማስገባት እና ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አቶ ከበደ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስረድተዋል፡፡

ወቅቱ የበልግ ወቅት በመሆኑ ወደ 2.7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በበልግ ለማልማት እቅድ መያዙን እና ከዛም ወደ 72 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኝበታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አንስተዋል፡፡

በበልግ ወቅት ሊገኝ የሚችለውን ምርት ለማግኘትም አርሶ አደሩ እንዲሁም ባለሙያው ሁሉም በመደጋገፍ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ አቶ ከበደ ላቀው ተናግረዋል።

በሐመረ ፍሬው

የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply