“የግብር አሠባሠብ ሥርዓቱን በማዘመን ዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመደገፍ እየተሠራ ነው” የገቢዎች ሚኒስቴር

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የገቢ አሠባሠብ ሂደቱን የሚያዘምን ዲጂታል የግብር ሥርዓት መገንባት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፋዊ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በዓለም ባንክ እና በገቢዎች ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ተወካዩች ተገኝተዋል። ውስብስብ የነበረውን የግብር አሠባሠብ ሂደት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ወደ ዲጂታል መቀየር የቻሉት ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ኬኒያ ተሞክሯቸውን በመድረኩ አካፍለዋል። […]

Source: Link to the Post

Leave a Reply