የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ አስጠነቀቁ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 21/07/13/ዓ.ም ባህር ዳር የግብጹ ፕሬዝዳንት ዓብዱልፈታሕ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በምትገነባው የሕዳሴ…

የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ አስጠነቀቁ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 21/07/13/ዓ.ም ባህር ዳር የግብጹ ፕሬዝዳንት ዓብዱልፈታሕ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በምትገነባው የሕዳሴው ግድብ ሰበብ የግብጽ የውሃ አቅርቦት የሚጓደል ከሆነ አጸፋው በቀጣናው ላይ ከባድ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ እንደ ሬውተርስ ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ ስለ ግድቡ በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ማንም እያስፈራራሁ አይደለም፣ ሁልጊዜም እኛ በምክንያታዊነት ነው የምንንቀሳቀሰው›› ያሉ ሲሆን ሆኖም ‹‹ማንም ቢሆን ከግብጽ ውሃ አንዲት ጠብታ እንኳ መውሰድ አይችልም›› ማለታቸውን አስነብቧል፡፡ አክለውም ይህ ከተፈጸመ በቀጣናው ላይ የሚያደርሰው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የራሷ ወንዝ በሆነው ዓባይ ላይ በምትገነባው የሕሴ ግድብ ላይ እስካሁንም ድረስ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር የሚደረገው ድርድር አለመጠናቀቁ የሚታወቅ ነው፡፡ በየወቅቱ አቋማቸውን የሚቀያይሩት ግብጽ እና ሱዳን በቅርቡ ባለሥልጣኖቻቸው አንዴ በካርቱም ሌላ ጊዜ ደግሞ በካይሮ ሲመክሩ መሰንበታቸውም ይታወሳል፡፡ በዚሁ ወቅት አገራቱ ወታደራዊ ስምምነትም አድርገው ነበር፡፡ ድርድሩን በተመለከተ ሱዳን ከአፍሪካ ኅብረት ተጨማሪ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያቀረበችውን ሐሳብ ግብጽ የደገፈችው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ አሁንም ድረስ ድርድሩ መቀጠል ያለበት በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ ነው በሚለው አቋም ጸንታለች፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply