You are currently viewing የግዮን በዓልን በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስታወቀ፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም       አዲስ አበባ ሸዋ የግዮን…

የግዮን በዓልን በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስታወቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የግዮን…

የግዮን በዓልን በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስታወቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የግዮን በዓል በየ ዓመቱ ጥር 13 በምዕራብ ጎጃም ዞን ሠከላ ወረዳ የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው ግሽ ዓባይ ከተማ ከአቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ የንግሥ በዓል ጋር በድምቀት ይከበራል፡፡ በሰከላ ወረዳ የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ ምንጭ ፣ ግሺ ተራራ ፣ የጉደራ ሐይቅ ፣ አርሲታ ዋሻ ፣ የፋሲል ግንብ (የአባ ግፍ ጅምር ግንብ) ፣ ትክል ድንጋዮች ፣ የአላዛር ዋሻ ፣ ድንጋይ ቀዳዳ እና ሌሎች የመስህብ ሃብቶች ይጎበኛሉ፡፡ በመጪው ጥር 13 ለአራተኛ ጊዜ ለሚከበረው የግዮን በዓል ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዓሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት የሚከበር ሲሆን ለዚህም በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ አስታውቀዋል፡፡ አቶ መልካሙ ምዕራብ ጎጃም ዞን የበርካታ የተፈጥሮ እና ሠው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዲያስፖራዎች እና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች በቦታው ተገኝተው የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ አቶ መልካሙ ዓባይ የአንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት ፣ የአብሮነታችን እና የጥንካሬያችን ማሳያም ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ አስተማማኝ ሠላም መኖሩን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው እንግዶችን ለመቀበል ሕዝቡም ሆነ የፀጥታ ኀይሉ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡ ዞኑ ከተፈጥሮና ሠው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻ በተጨማሪ መልማት የሚችል ለም መሬት፣ ዓባይን ጨምሮ ክረምት ከበጋ ሳያቋርጡ የሚፈሱ ወንዞች የሚገኙበት፣ ታታሪ እና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለቤት በመሆኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡ አቶ መልካሙ ሕዝቡም በህልውና ዘመቻው ያሳየውን አንድነት እና መተባበር በበዓሉ አከባበር ላይ እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የባህር ዳር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply