You are currently viewing #የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው ፍ/ቤቱ ነፃ ብሎ ብይን ቢሰጥም ከእስር እንዳይፈታ ተከለከለ! ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው የባህር ዳር…

#የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው ፍ/ቤቱ ነፃ ብሎ ብይን ቢሰጥም ከእስር እንዳይፈታ ተከለከለ! ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው የባህር ዳር…

#የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው ፍ/ቤቱ ነፃ ብሎ ብይን ቢሰጥም ከእስር እንዳይፈታ ተከለከለ! ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግፍ እስረኛው አብርሃም አደራጀው የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ3 ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ቢወስንም <<ከበላይ አካል በታዘዘ ትዕዛዝ እንዳትለቁት ተብሏል >>በሚል ህገ – ወጥ አካሄድ እስከ ዛሬ ድረስ በግፍ እሰር ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ ‼️ አብርሃም አደራጀው በማህበራዊ የትስስር ገፁ መጠሪያ <አብርሃም አደራጀው አማራው > በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ላይ ፊት ለፊት መንግስታዊ ስርዓቱን በማህበራዊ የትስስር ገፁ የሚሞግት ፤ለአማራ ህዝብ ብለው በአራቱም አቅጣጫ በግፍ ለሚታሰሩ ፣ስቃይን ለሚቀበሉ እንዲሁም ለሚሳደዱ ሁሉ ደምፅ የሚሆን እና በግፍ ታስረው ባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ለሚታሰሩ የአማራ ህዝብ ታጋዮች ሳይታክት በማረሚያ ቤት በመገኘት የሚያበረታታ ንቁ የባህር ዳር ከተማ ወጣት ነው ። ነገር ግን አፋኙ ስርዓት ይህንን ወንድማችንን በግፍ እስር ውስጥ ካደረገው ሳምንታት ተቆጥረዋል ።የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በ3ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ቢወስንም ከበላይ አካል በታዘዘ በሚል ተልካሻ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ በግፍ እስር ላይ ይገኛል ። በዛሬው ዕለትም በባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበ ቢሆንም ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይሰጠው ድጋሜ ለነገ ማለትም ጥር 19/2015 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዐት ቀጥረውታል ። በመሆኑም በአራቱም ማዕዘን የምንገኝ የግፍ እሰርን የምናወግዝ ሁሉ ለወንድማችን አብርሃም አደራጀው ድምፅ ልንሆነው ይገባል ።በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ግፍን የምታወግዙ ሁሉ ነገ ጠዋት 4:00 ሰዐት በባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመገኘት ያለንን አማራዊ አንድነት ፣አብሮነት እና ወንድምነት እንገልፅ ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጥሪው ያስተላልፋል ። በማዋከብ ፣በማሰር እንዲሁም በማሳደድ የሚቆም ፣የተጀመረ የአማራ ትግል ፈፅሞ የለም ።የትግላችን ማዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል ‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply