የጎርጎራ ፕሮጀክት የሚካሄድበት ስፍራ ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው

የጎርጎራ ፕሮጀክት የሚካሄድበት ስፍራ ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎርጎራ ፕሮጀክት የተሳለጠ እንዲሆን የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደር የፕሮጀክቱን ስፍራዎች ከሶስተኛ ወገን ነጻ እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው ጎርጎራ በአጭር ጊዜ ለማልማት የሚያስችለው ዝግጅት ከመጀመሩ የባለሀብቶች ዓይን ማረፊያ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

በጎርጎራ ከወዲሁ በርካታ ባለሀብቶች በስፍራው ለማልማት ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው ተብሏል፡፡

ጎርጎራን ለማልማት በተጀመረው ፕሮጀክት በስፍራው ምልከታ ያደረገው የባለሙያዎች ቡድን በበቂ ጥናት በአነስተኛ ወጪ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያችል መሆኑን ተመልክቷል።

የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደርም ከወዲሁ ታጥረው የነበሩና ልማት ያልተካሄደባቸውን ቦታዎች በመለየት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች የመስጠት ስራም ጀምሯል፡፡

በከተማዋ በርካታ መሬት ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን ፕሮጀክቱ በትክክል የሚያርፍበት ቦታ ሲረጋገጥ የሚጠየቁ ተጨማሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ዝግጅትም ተደርጓል።

በፌደራል መንግስት እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች እንዳሉ ሆነው የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በፕላን ስራው ላይ የሚያስፈልገውን እገዛ ለማድረግ የሚችል የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስራ አስገብቷል።

ዩኒቨርሲቲው እድሜ ጠገቧን ከተማ በፕላን እንድትመራ የማድረግ ሀላፊት የተሰጠው ሲሆን በየዘርፉ የሚመለከተውን ባለሙያ ማካተቱም ተገልጿል፡፡

የአውደ ጥናት ዝግጅት የሀብት ማስተዋወቅና ግንዛቤ መፍጠር ስራም በዩኒቨርሲቲው ተጀምሯል።

ሂደቱን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ከተማዋን የወደፊት እድገቷንና ፕሮጀክቱን የሚመጥን ፕላን እንዲኖራት ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፕሮጀክቱ ከእውቀት ባለፈ በገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።

 

በሀይለኢየሱስ ስዩም

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የጎርጎራ ፕሮጀክት የሚካሄድበት ስፍራ ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply