የጎንደር ሰላምና ልማት ማህበር ዘላቂ ሰላምን በተመለከተ የምክክር ጉባኤ አካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጎንደር ሰላምና…

የጎንደር ሰላምና ልማት ማህበር ዘላቂ ሰላምን በተመለከተ የምክክር ጉባኤ አካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጎንደር ሰላምና ልማት ማህበር /ጎ. ሰ.ማ/ “አብሮነት ለውስጥ ጥንካሬ፣ የውስጥ ጥንካሬ ለሰላምና ልማት፣ ሰላምና ልማት ለሀገር ህልውና” በሚል መሪ ቃል ስለጎንደር ብሎም ስለሀገር አቀፍ ሰላምና እድገት እንዲሁም ስለህልውና ዘመቻው አጠቃላይ ተጋድሎ ትኩረት ያደረገ የምክክር ጉባዔ ታህሳስ 17/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ዞን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢንዱስትሪ ሚ/ር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚና የማህበሩ የበላይ ጠባቂ አቶ መላኩ ፈንታ፣ የ ጎ.ሰ.ማ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ በላቸው፣ የአማራ ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ፣ የ ጎ.ሰ.ማ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አቶ ወርቁ ለምለሙ፣ የፖለቲካ ፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እንዲሁም ከጎንደር፣ ከባህርዳር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን፣ የክልልና የዞን አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለሀብቶች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ታድመዋል ተብሏል፡፡ “ወንድማማችነት ለኢትዮጵያ የሀገራዊ ህልውና መፅናት መሰረት መሆኑን ከታሪካችን ተምረንና አሁንም በጋራ ከመስራትና ከመደራጀት በቀር ሌላ አማራጭ የለንም” ሲሉ የ ጎ.ሰ.ማ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አቶ ወርቁ ለምለሙ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው አንስተዋል፡፡ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ሀይል የፈፀመብንን የግፍ ወረራ ቀልብሰን በአሸናፊነት ድል ባስመዘገብንበት ማግስት ይህ ጉባኤ መካሄዱ ታሪካዊ እንደሚያደርገው የፌዴሬሽን ም/ ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልፀዋል፡፡ በዚህ ዘላቂ ሰላምን ስለማስፈን ትኩረት ባደረገው ጉባዔ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል። በዚህም መሰረት ስለጎንደር ሰላም መልካም አጋጣሚወዎች፣ተግዳሮቶችና መፍትሔወች በዶ/ር ሲሳይ ምስጋናው ፣ ስለ ጎንደር ልማት በረ/ፕሮፌሰር ገናናው አግተው፣ እንዲሁም ስለጎንደር ሰላምና እድገት ማህበር /ጎ.ሰ.ማ/ አመሰራረትና መዋቅራዊ አደረጃጀት በተመለከተ በኢንጂነር በሪሁን ካሳው ጥናታዊ ፅሁፎችና ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡ በመጨረሻም በቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ጉባኤው ተጠናቋል ሲል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply