የጎንደር እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች ከተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበራቸው…

የጎንደር እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች ከተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበራቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሀገራችን እና በሌሎች ሀገራት እና በተቋማትም ጭምር በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። በዓሉ በድምቀት ከተከበረባቸው ተቋማት መካከል የጎንደር እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲዎች ተጠቃሽ ናቸው። ዩኒቨርስቲዎቹ መምህራን እና የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ከተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበራቸውን አስታውቀዋል። የዩኒቨርስቲው ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት እንደገለጸው በጎንደር ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሩ እና በየደረጃው ያሉ የተማሪ አስተባባሪዎችና የተማሪዎች ተወካይ በዓሉን ባማረ መልኩ እንዲከበርና ተማሪዎች ቤታቸው ያሉ ያክል እንዲሰማቸው ቤት ውስጥ የሚደረጉ የበዓል ድባብ በመፍጠር መሳተፋቸው ተገልጧል። በዓሉን ከተማሪዎች ጋር እያሳለፉ ለሚገኙ የምግብ ቤት ሰራተኞች ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች፣የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ከተማሪዎች ጋር በመሆን የእየሱስ ክርስቶስ ልደትን አክብረዋል። በፕሮግራሙ የተገኙት የአስተዳደር ልማት ም/ፕሬዚደንት ልዩ አማካሪ የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክንድየ አይችሉህም ተማሪዎች በዓሉን በዚህ መልኩ ማሳለፋቸው ከወላጅ ጋር የነበራቸውን ትውስታ በመርሳት በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ከማድረጉም በላይ ተማሪዎች በአንድነትና በመተሳሰብ መንፈስ ለሀገራቸው ሰላም እንዲቆሙ ያስችላቸዋል ብለዋል። የተማሪወች ህብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ ፍቅሩ ባይለየኝ በበኩሉ በዓሉን በደስታ እንድናሳልፍ ላደረጉት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ፣ ሰራተኞች በተለይም ቤታቸውን ትተው ከእኛጋር ሌሊቱን ሙሉ ምግብ እና ሌሎች መስተንግዶዎችን ላዘጋጁልን እናቶችና እህቶች ምስጋናችን ከፍ ያለነው ሲል አስተያየት ስለመስጠቱ የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply