የጎንደር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች በመጠጥ ውሃ ችግር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል

የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ባዩ አቦሃይ ለጣቢያችን እንዳሉት የከተማዋ ነዋሪዎች በከፍተኛ በመጠጥ ውሃ ችግር ላይ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

ጎንደር ከተማ በየቀኑ 70ሺህ ሜትር ኪዮብ ውሃ ብትፈልግም ለከተማዋ በአሁኑ ስዓት እየቀረበ የሚገኘው ግን 13 ሺህ ሜትር ኪዮብ ውሃ ብቻ በመሆኑ ነዋሪዎቿ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ነው ያሉት።

አቶ ባዩ በፌድራል የውሃ ሚኒስተር ቡድን ተዋቅሮ በሶስት ምዕራፍ በአጭር ፣በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚጠናቀቅ ፕሮጀክት መጀመሩን ገልፀዋል።

ከዚህም አቅድ መካከል የአጭር ጊዜው እቅድ ተግባራዊ ሆኖ በ20 ቀን አንዴ ውሃ ያገኝ የነበረውን የከተማ ነዋሪ አሁን በመደበኛ ነት በ15 ቀን አንዴ እንዲያገኝ እየተሰራ ነው ብለዋል ።

አቶ ባዩ አጠቃላይ የውሃ ስርጭት በከተማዋ ውስጥ 18 በመቶ አንደሆነም ነግረውናል

የረጅም ጊዜ እቅዶች በተለያዩ ምክንያቶች በመጓተታቸው በነሱ ውጤት ማምጣት አልተቻለም ነው ያሉት።

አቶ ባዩ አቦሃይ በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ትላልቅ ተቋማት ኢንዱስትሪዎች ፣ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን የውሃ ማግኛ መንገድ እንዲፈጥሩ ለመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም እየተደረገ ነው ብለዋል።

በከተማዋ ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርም ከተማዋ የምትታወቅበት የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰ እንደሚገኝም ነው የተጠቆመው።

በቀጣይ አሁን ያለው የውሃ ችግር በዚሁ ከቀጠለ እና አፋጣኝ መፍትሔ ካልተሰጠው የከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ተብሏል ።

በመጨረሻም 17 የውሃ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ወደተግባር እንዲገቡ ለማስቻል ፈንድ የማፈላለግ ስራ አየተሞከረ ነው ብለዋል።

ልዑል ወልዴ
መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply