የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በንፁህ መጠጥ ዉሃ እጥረት መቸገራቸውን ተናገሩከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ ማነስ በየዕለቱ ምግብ ለመስራትና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/aLbcT3HStfyDLTeg40ORlEsDi3Ia7SA8H6CsjsGXBJjPKfGT7G1BI8LCcXdzl7QUf3PJzV1rYUbJg_8ZJz6c6ySllTb7l54G9CCBnJCpWmM0rk8AXFZSYJR96ocpkFryOQ_0H0WoL1xSEGuVMNVvR_0Jim05rH7gEl53GgS0xrmcYVYOLjDcBctx6QxFyFVo1eooX7ZXAS-_H7-dIHs8xjTNZCLwfEyPcELahEFspSfUwLpwmMvdOgiWXPtjozrQw8fOKges3NI2kRlHJzjjbvAVgR3fLDc1akiIpeCg6R3_T1xTICbGAq4YlAOlMPqgC_LSYbBM9oKs8r-XoVOgnQ.jpg

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በንፁህ መጠጥ ዉሃ እጥረት መቸገራቸውን ተናገሩ
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ ማነስ በየዕለቱ ምግብ ለመስራትና ንፅህናን መጠበቅ አልቻልንም ብለዋል፡፡

ከአመታት በፊት ጀምሮ ውሃ በየሰፈሩ በጥቂት ቀናት ልዩነት ይመጣ እንደነበር ያስታወሱት ነዋሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ግን ከወር በላይ ውሃ እንደማይገኙ ተናግረዋል።

በዚህም ለከፍተኛ ችግር እንተጋለጡ ነዋሪዎቹ ነግረውናል።

ከነዋሪዎች በተጨማሪም የጤና ተቋማት በአግባቡ ስራቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ሰምተናል፡፡

የጎንደር ከተማ የውሃ አገልግሎት ፅህፈት ቤት በበኩሉ፤ ችግሩ መኖሩን አምኖ መፍትሄ ለማምጣት ከክልሉና ከፌዴራል መንግስት ጋር እየሰራሁ ነው ብሏል።

የፅህፈት ቤቱ ዉሃና ፍሳሽ የደንበኞች አገልግሎት የስራ ሂደት መሪ አቶ ታምራት መኩሪያ የፕሮጀክቶች መዘግየት ለችግሩ ዋነኛ ምክንያት ነዉ ብለዋል፡፡

የውሃ ጉድጓዶችን በመጥረግ የውሃ አቅም የማጠናከር ተግባር እየተሰራ መሆኑን ነግረዉናል።

በክልሉና በፌድራል መንግስቱ የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ እቅድ ተይዞ እንዲሰራ በተቀመጠው አቅጣጫ ጥረት እየተደረ እንደሆነ አቶ ታምራት አንስተዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 11ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply