የጎጃም አማራ ፋኖዎች ከግንባር ወደ ውቢቷ ባህርዳር ሲገቡ በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

የጎጃም አማራ ፋኖዎች ከግንባር ወደ ውቢቷ ባህርዳር ሲገቡ በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራን ሊወር ሊደፍር እና ሊያዋርድ የመጣውን የትግራይ ወራሪ ሃይል ከመካነ ሰላም እስከ ቆቦ ድረስ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብድ የሰሩት የጎጃም አማራ ፋኖዎች ወደ ውቢቷ ባህርዳር ሲገቡ የጀግና አቀባበል ተደረጎላቸዋል። በአቀባበል ፕሮግራሙ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣የባህርዳር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ የኔሰው መኮንን፣የአማራ ክልል ሚኒሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮ/ል ባምላኩ አባይ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል። የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ጀግኖቻችን የናንተን ውለታ መቸውም ቢሆን አገሪቱም ይሁን ህዝባችን አይዘነጋውም ደማቅ ታሪክ ነውና የጻፋችሁ ፋኖ ማለት ሃገር ስትደፈር ቀድሞ የሚገኝ የሃገር ባለውለታ ነው ይሄንን ታሪክም በኛ ዘመን እናንተ አስቀጥላችኋልና ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል። ክልላችን ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩሀይልና በየደረጃው ከሚገኘው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጠላትን ድባቅ በመምታት ለዚህ ድል ስለበቃችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የጎጃም አማራ ፋኖ መሪ መቶ አለቃ አሰፋ አድማሱ ለተደረገላቸው አቀባበል በማመስገን ላለፉት ወራቶች ከጎናቸው በመሆን እንደ አባት እና እንደ አለቃ በመታዘዝ ታላቅ ጀብዱ የፈጸሙ የፋኖ አባሎችን ዛሬ ያጠናቀቅነው የመጀመሪያ ዙር ዘመቻችንን እንጂ የመጨረሻችን አይደለም ብለዋል። ስለዚህ ለቀጣይ ግዳጅ እንዘጋጅ ወራሪው ሃይል አማራን ሳያጠፋ እንቅልፍ አይተኛምና እኛም ነቅተን መጠበቅ አለብን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በክቡር ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ አማካኝነት የቀደሞ ጀግና የኢትዮጵያ መሪዎች ምስል ለዘመኑ ጀግኖች በክብር ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የባህር ዳር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply