የጠለምት ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በአስቸኳይ ወደ ወረዳው እንዲገቡ የወረደው አስተዳደር ጥሪ አቀረበ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

የጠለምት ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በአስቸኳይ ወደ ወረዳው እንዲገቡ የወረደው አስተዳደር ጥሪ አቀረበ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጠለምት ወረዳ ባለው ነባራዊ ሁኔታ በየደረጃው ያለውና አመራር ከቦታው ተፈናቅሎ ቆይቷል። ይሁን እንጂ አብዛኛው አመራርና ውስን ባለሞያዎች ከአካባቢው ወጣቶችና ማህበረሰቦች ጋር በመሆን በመቀናጀት በጸጥታ ስምሪት፣ የልማትና የህዝብ ግንኙት ሥራዎችን በማከናወን ከነሐሴ 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ መልሶ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል። የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ወረታ በደብዳቤ እንዳሳወቁት በጸጥታ ስምሪት፣ የልማትና የህዝብ ግንኙት የሚከናወኑት ከመደገፍ ይልቅ ደመወዝ እየተከፈለው በየአካባቢው የተደበቀው የመንግስት ሠራተኛ በአስቸኳይ ወደ ወረዳው ጥሪ አቅርበዋል። የወረዳው አርሶ አደሮች ከማሳው ከውስን(5) ቀበሌዎች ውጭ ከሰጋት ነፃ ሆኖ ማሳውን መንከባከብ ችሏል። አሸባሪው ጁንታ እንደፈለገ የማያልፍባቸው በሮች መኖራቸና የሚሠራው ፕሮፖጋንዳ ኪሳራ የገጠመው መሆኑ፤ የጠለምትን ህዝብና የታጣቂ ጏይል መዋጋት ከአቅሙ በላይ መሆኑን አረጋግጧል። የወረዳው ህዝብ፣ የጸጥታ መዋቅርና አመራር ጠላትን ለመመከት ቁርጠኛ አቋም እንዲወስድ ምቹ ሆኔታ ተፈጥሯል በማለት አቶ መርሻ ገልጸዋል። በመሆኑም የወረዳው አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የወረዳው ነዋሪዎች ችግሮችን መቋቋም የተቻለው በመደራጀት ነው። ስለዚህ ከየአቅጣጫው ተበታትናችሁ የምትገኙ የሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ የወረዳው አመራሮችና የቀበሌ ባለሙያዎች እሰከ ኅዳር 5/2014 ዓ.ም በወረዳው ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል። በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ወደ ወረዳው ፈጥኖ ለመመለስ የሚቸገሩ ለሰሜን ጎንደር ዞን የመንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ብታሳውቁና ወክለን ለምናስቀምጠው ሪፖርት ብታደርጉ፤ ወደ ወረዳው ስትመለሱ አሰፈላጊ ለእለት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እንድታመጡ የሚል መልዕክት ወረዳ አስተዳዳሪው አስተላልፈዋል። ለማይገኘው ግን ደመወዝ መስራት እንደማይችሉ አሳውቀዋል። የሚመለከታቸው የበላይ አመራሮች የመገናኛ (የስልክ)፣ የሬሽን አቅርቦት፣ በተደጋጋሚ የሚጠየቁትን ወታደራዊ ግብዓቶችና የተቀናጀ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸውም አሳስበዋል። መረጃው የጠለምት ወረዳ አስተዳደር መሆኑን ገልጾ የዘገበው የሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply