የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪና የኢትዮጵያውያን ምላሽ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም. ድረስ እንዲገቡ ያቀረቡትን ጥሪ ተክትሎ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው እየተነገረ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ትናንት ባሰሙት መልዕክት ኢትዮጵያውያኑን እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

በመልዕክታቸውም “የተጎዱ አካባቢዎችን እንድትጎበኙ፤ ወገናችሁን እንድታንጹና እንድትደግፉ አደራ እላለሁ። አሸባሪው ህወሓት በወገናችን ላይ ያደረሰውን ልክ የሌለው ግፍና መከራ በዓይናችሁ አይታችሁ ዓይኔን ግንባር ያርገው ላለው ዓለም እንድትገልጡ ላሳስባችሁ እወዳለሁ። አንዳንድ ተቋማት ባዘጋጇቸው መርሐ ግብሮችም ላይ ተሳተፉ። የቱሪስት መዳረሻዎችንም ጎብኙ። የልማት ሥራዎቻችንንም ተመልከቱ” ብለዋል፡፡

የኮሎምቦስ ኦሃዮ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኮርሶ ኮጂ ጥሪውን ተቀብለው በሚቀጥለው ሳምንት ወደዚያው እያመሩ መሆኑን ሲገልጹ፣ የሜሪላንድ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተስፋሁን ካህሳይ ደግሞ የጉዞውን ዓለማና ጉዞው የሚደረግበትን ወቅት የማይደግፉ በመሆኑ እንኳን እሳቸው ሊሄዱ ሌሎች ተሳታፊ እንዳይሆኑ የሚፈልጉ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ 

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply