You are currently viewing “የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ወደ መንበረ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ አማራው ሞትን በመላመድ ላይ ይገኛል!! ስርዓቱ በንፁሃን አማሮች ደም መቆመሩን ማቆም አለበት!!” የአማራ ፋኖ አንድነት…

“የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ወደ መንበረ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ አማራው ሞትን በመላመድ ላይ ይገኛል!! ስርዓቱ በንፁሃን አማሮች ደም መቆመሩን ማቆም አለበት!!” የአማራ ፋኖ አንድነት…

“የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ወደ መንበረ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ አማራው ሞትን በመላመድ ላይ ይገኛል!! ስርዓቱ በንፁሃን አማሮች ደም መቆመሩን ማቆም አለበት!!” የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ “የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ወደ መንበረ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ አማራው ሞትን በመላመድ ላይ ይገኛል!! ስርዓቱ በንፁሃን አማሮች ደም መቆመሩን ማቆም አለበት!!” ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አሳስቧል። በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሱ ላሉ የዘር እልቂቶች የአማራ ብልጽግና መንግስት በዋናነት ተጠያቂ ይሆናል ሲልም ገልጧል። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በወቅታዊ ጉዳይ ያወጣው መግለጫ:_ ሰኔ 11/10/2014 ዓ.ም ኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በንፁሃን አማሮች ላይ በአሸባሪው ኦነግ ሼኔ የተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ልባችን ሰብሮታል!! ይህን እኩይ ድርጊት ሰው የሆነ ሁሉ ሊያወግዘው ይገባል። ኦነግ ሸኔን እና የህወሓትን ወራሪ ሃይል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግስት አሸባሪ ብሎ የሰየመ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በመደበኛ ህግ የተፈረጁ መደበኛ አሸባሪ እንጂ ኢ-መደበኛ አይደሉም!! ጠዋት ማታ በንፁሃን አማሮች ደም የምትታጠበው ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የሚፈፀመው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ አሁን ብቻ አይደለም። ቆይትም ብሏል!! በኦነግ ሸኔ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ አቃሎ ማየት፣ አለባብሶ መጥራት ብሎም በዚሁ አሸባሪ ቡድን ላይ ተገቢውን እርምጃ ያለመውሰድ ሌላ ተጨማሪ ወንጀል ነው። ይህ ብቻ አይደለም የአማራን ህዝብ እንደ መናቅም ይቆጠራል። መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ከመንግስት ዝቅተኛ ተግባራት መካከል ህግ በማስከበር የዜጎችን የደህንነት ዋስትና ማረጋገጥ ነው። በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ወደ መንበረ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ አማራው ሞትን በመላመድ ላይ ይገኛል!! ስርዓቱ በንፁሃን አማሮች ደም መቆመሩን ማቆም አለበት!! የአዞ እምባ የሚያነቡት እራሳቸውን የሃይማኖት ተቆርቋሪዎች ነን ብለው የሚያስቡ አክራሪ ሃይሎች(ዑስታዝ አሕመዲን ጀበል) ልሳን የመዘጋት፣ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ፀጥ የማለት ሁኔታ አማራዎች ከአማራ ክልል ውጭ መታረዳቸው ዶሮ የታረደም ያህል ሊሰማቸው ባለመቻሉ እጅግ ታዝበናል!! በአራቱም አቅጣጫ በእሳት ቀለበት ከበባ ውስጥ ያለው አማራው ነው። የአማራ ማህበረሰብ በየጊዜው ከመኖሪያ ቀዬው ተፈናቅሎ ይሰደዳል፣በጅምላ ይጨፈጨፋል፣በጠላትነት ተፈርጆ ይታደናል፣ሃብትና ንብረቱን ይዘረፋል፣አማራነቱን እስኪጠላ ድረስ እየተሸማቀቀ ይገኛል ወዘተ የዚህ ሁሉ መነሾ ከህገመንግስቱ የተቀዳው የመንግስት ስርዐት እንደሆነ እናምናለን!! አማራ እንደ ህዝብ ተከብሮ በሰራትና በአኖራት ኢትዮጵያ መኖር እንዳይችል ትልቅ ፈተና ሆኖበታል!! በአሸባሪዎች ዘንድ የአማራ ህዝብ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲደርስበት ሌሎች ወንድም ህዝቦች ተመልካች መሆናቹህ አሳፋሪ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የምትቀጥለው ህዝቦቿ እንደ አንድ ህዝብ መኖር ሲችሉ ብቻ እንደሆነ እንረዳለን። በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሱ ላሉ የዘር እልቂቶች የአማራ ብልጽግና መንግስት በዋናነት ተጠያቂ ይሆናል። ምክንያቱም የአማራ ብልጽግና መንግስት የወከለውን ህዝብ ማንነቱንና ነፃነቱን የማስከበር ህጋዊ ግዴታ አለበት!! ስለሆነም የአማራ ብልጽግና የአማራን ንፁሃን ደም መፍሰስ ለማስቆም የአማራ የግድያን ቀመር ያገናዘበ ትግል ማድረግ እንዳለበት እናምናለን!! በወለጋ ዞን በቶሌ ቀበሌ በኦነግ ሸኔ በንፁሃን ህፃናት እና ሴቶች ላይ የተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ሰይጠናዊ ድርጊት በኢትዮጵያዊነታቸው ሊደራደሩ ባማይችሉ የጎንደር፣የወሎ፣የጎጃም፣የሽዋና የአዲስ አበባ አማራዎች ላይ እንደሆነ እንረዳለን። ስለሆነም የአማራ ጉዳይ ያገባኛል የምትሉ አካላት በሙሉ ከአማራ ክልል ውጭ በሚኖሩ አማራዎች ጉዳይ ላይ ጥልቅ የሆነ ክልላዊ ምክክር መደረግ አለበት ብለን እናምናለን። ተወያይተን ከሚደርስብን ማንነታዊ የጥቃት ቀለበት ውስጥ መውጣት ካልቻልን አደጋው ከባድ ሆኖ ይቀጥላል። በሶሻል ሚዲያ የሃዘን እንጉርጉሮ መፍትሄ ሆኖ እንደማይቀጥል እናውቃለን። የተጨፈጨፉ ወገኖቻችን ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን !! ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply