የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኬንያ የስራ ጉብኝትን እና ከፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉትን ምክክር ተከትሎ የኬንያ ” ስቴት ሀውስ ” የጋራ ነው ያለውን መግለጫ ትናንት አመሻሽ አውጥቷል።

በዚህም መግለጫ ፤ ፕሬዚዳንት ሩቶ እና ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ከአፍሪቃ ቀንድ ደህንነት ጋር በተያያዘ ፤ በአህጉሪቱ ውስጥ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ማስጠበቅ ለኢኮኖሚ እድገትና ልማት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸው ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ፤ ለሀገራት ግዛቶች ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እውቅና መስጠት ሉዓላዊነታቸውን ማክበርና ማስከበር እንደሚገባ ተነጋግረዋል።

ሕገ መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦችን እንዲሁም በአፍሪካ አገሮች የውስጥ ፖለቲካ የውጭ ጣልቃ መግባት እንደማይቀበሉት ገልጸዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ መሪዎቹ ፤ ሁለቱ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ አሳ ሀብት፣ ትራንስፖርት፣ አይሲቲ፣ ቱሪዝም፣ ጤና፣ ባህል እና ደን ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply