የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮረናን በመከላከል ዘመቻ እና በትሕነግ ላይ በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ወቅትም ከተጎዱት ወገኖች ጎን በመቆም ያሳየውን ማህበራዊ ተሳትፎ እና የጀመረውን ቅንጅ…

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮረናን በመከላከል ዘመቻ እና በትሕነግ ላይ በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ወቅትም ከተጎዱት ወገኖች ጎን በመቆም ያሳየውን ማህበራዊ ተሳትፎ እና የጀመረውን ቅንጅ…

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮረናን በመከላከል ዘመቻ እና በትሕነግ ላይ በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ወቅትም ከተጎዱት ወገኖች ጎን በመቆም ያሳየውን ማህበራዊ ተሳትፎ እና የጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል በጎንደር በነበረው ቆይታ ወደ ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማቅናት የተቋሙን እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ከተቋሙ አመራሮች ጋር ቆይታ አድርጓል። በተለይም የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተቋማዊ ተግራት ብቻ ሳይታጠር በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፎች በሚያደርገው እንቅስቃሴ እና በተሻለ ቅንጅታዊ አሰራሩ ይታወቃል። ይህ መልካም እንቅስቃሴው ኮሮናን ለመከላከል ባደረገው ዘመቻ፣ በትህነግ ላይ በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ወቅት ለተጎዱ ወገኖች የህክምና አገልግሎት፣ በፀጥታው ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ለልዩ ሀይል አባላት የምስጋና ፕሮግራም በማዘጋጀትና በሌሎች ዘርፎች በንቃት ሲያደርገው በነበረው ተሳትፎ ይገለጻል። ተቋሙ ለዚህ አርዓያነት ያለው ስራውም እንደአብነት ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል። ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ በሙያው ዘርፍ ላደረገው አስተዋፅኦም የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል እውቅና የሰጠው መሆኑ ተገልጧል። ቅንጅታዊ አሰራሩንና በጎ ማህበራዊ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት የገለፀው ተቋሙ በርካታ እቅዶችን ለማከናወን መዘጋጀቱን አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ወደ ጠዳ በማቅናት ከጤና ሳይንስ ኮሌጁ ዲን ከዘመነ ሀብቱ እና ከአካዳሚክ ምክትል ዲኑ ከአስናቀው አስረስ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርጓል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply