የጠገዴ ወረዳ ፍ/ቤት በሰው ማገት ወንጀል በተሰማራ ግለሰብ ላይ የ8 ዓመት ከ4ወር ፅኑ እስራት መወሰኑን የጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህ…

የጠገዴ ወረዳ ፍ/ቤት በሰው ማገት ወንጀል በተሰማራ ግለሰብ ላይ የ8 ዓመት ከ4ወር ፅኑ እስራት መወሰኑን የጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህ…

የጠገዴ ወረዳ ፍ/ቤት በሰው ማገት ወንጀል በተሰማራ ግለሰብ ላይ የ8 ዓመት ከ4ወር ፅኑ እስራት መወሰኑን የጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ተከሳሽ አቶ እንየው ደጀን የጠገዴ ወረዳ ሸኒ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 586 እና 590 (2) (ሐ) በመተላለፍ ተከሳሽ ሰኔ ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ጠገዴ ወረዳ ሸኒ ቀበሌ ሽንጥሮ አባ ከተባለ ቦታ የግል ተበዳይ የሆኑት አቶ ሁናቸው ጣሰውና ዋኘው ይመር የእርሻ መሬታቸውን አይተው በመመለስ ላይ እንዳሉ አግቷል። በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ሶስት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን መሳሪያ ተኩስ በማስፈራራት ነው ወደ ዝግባ ቀበሌ ወስደው በማሰር ከቤተሰባቸው ጋር በመደራደር ሰኔ 25/2012 ዓ.ም 150 ሺህ ብር በመቀበል በፈፀመው የሰው ማገት ወንጀል ተከሷል። ተከሳሹ ታህሳሰ 6/2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ የአቃቢ ህግ የክስ ቻርጅ ተነቦለት ክሱን አልቃወምም ድርጊቱን ግን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም በማለት ክዶ በመከራከሩ የአቃቢ ህግ ምስክሮች ተሰምተዋል። ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመው ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በተደረገ ስምምነት በመሆኑ፣ከዚህ ቀደም የጥፋተኝነት ክስ የሌለበትና በወንጀል ህግ ቁጥር 82 (1) (ሀ) መሰረት የቀደመ የዘወትር ፀባዩ መልካም እንደሆነ ተቆጥሮ ተከሳሹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ በወንጀል ህግ ቁጥር 86 መሰረት ሁለት ማቅለያዎች ተይዘውለታል። በመሆኑም የጠገዴ ወረዳ ፍ/ቤት ታህሳስ 6/2013 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛውን ያስተምራል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ያለውን ቅጣት አስተላልፏል። ይኸውም ተከሳሹ ከተያዘበት ከጥቅምት 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ8 ዓመት ከ 4ወር ፅኑ እስራት መወሰኑን በጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ደብሪቱ ምትኩ ጎበዜ መረጃውን አድርሰውናል ሲል የወረዳው ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply