የጠ/ሚኒስትሩ ጥሪ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ

https://gdb.voanews.com/81547d5c-9da6-4021-91af-b94098c5e2dc_tv_w800_h450.jpg

በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የ”ወደ ሃገር ቤት እንግባ” ጥሪን እንዲቀላቀሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጠይቀዋል።

ጥሪው በገና በዓል አካባቢ የሚኖረውን የእረፍት ጊዜ በመጠቀም አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያን ትውልደ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሃገር ቤት እንዲመጡ የተጋበዙበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ቢል ለኔ ስዩም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል ።

የእነርሱ በብዛት መምጣት የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ለማሳየት እንደሚያግዝም ነው ቢል ለኔ ያመለከቱት።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ክፍል ሃላፊ የሆኑትን ቢል ለኔ ስዩምን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply