የጡረት አበል የተከለከሉ የትግራይ ክልል ጡረተኞች ለችግር መዳረጋቸው ተነገረ፡፡የትግራይ ጡረተኞች ከ2013 ሐምሌ ወር አንስቶ እስከ ታህሳስ 2015 ዓ.ም የውል አበል ክፍያ እንዳልተ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/L5_-WAT-fLw256p2pFBR8LwSGMizoSxUs2VoWHH73gDK-DsJF348wBO7D2sEzNm7kI08lMPLHB6q9h2vtASSFjCeNK63oY-jzAPrN5r7WW2VtWZSoU9a6wECTpg6OiYA9JblDtI0VzADEedN2yiKkHIH_0c1bGMr9emjAAsFIKWz7xFMeBKA7Y1C7UyAIP5poi2RzwUySiTuVpr-OHPVqxFa9QQ7UYx5daXkOg07uQFZ5FjHnCNKYUPAoaQXE9NvSmlmklcIuOO6qyoXCCRo_yWxMMYGDqvlHRNSi3Jzf6Vd63C5WQrJD8Ynz3WM2OPK_wxe8W1BoSlqPD0bID1p8g.jpg

የጡረት አበል የተከለከሉ የትግራይ ክልል ጡረተኞች ለችግር መዳረጋቸው ተነገረ፡፡

የትግራይ ጡረተኞች ከ2013 ሐምሌ ወር አንስቶ እስከ ታህሳስ 2015 ዓ.ም የውል አበል ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ማህበሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

የመቀሌ ጠረተኞች ማህበር ሊቀመንበር ዶክተር ገብረሚካኤል ንጉሴ ለጣቢያችን እንደተናገሩት የ18 ወራት ውዝፍ የጡረታ አበል ክፍያ ሊከፈላቸው አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ባሳለፍነው የካቲት 21/2016 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎችን ቢያካሂዱም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

“በመንግሰት አዋጅ በመከልከሉ እስከሚፈቀድ ጠብቁ” እንዲሁም “በክልል ያልተከፈለ ክፍያ ስላለ ክፍያው ሳይፈፀም በጀቱ አይለቀቀም”በሚሉና በሌሎችም ምክንያቶች ክፍያው ሊከፈላቸው አለመቻሉን ሊቀመንበሩ አስረድተዋል ፡፡

በአሁን ሰዓት በክልሉ የሚታየው መጠነ ሰፊ ችግር ለጡረተኞች ነገሮችን ይባስ እንዲከፋባቸው እንዳደረገባቸው ተነስቷል፡፡

የካቲት 21 በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የትግራይ ጡረተኞች ድምፅ ይሰማ፣ የ18 ወራት ውዙፍ አበል በአስቸኳይ ይከፈለን እና የፕሪቶሪያ ውል በአስቸኳይ ይተግበር በሚሉ መፈክሮች ጉዳዩ መልስ እንዲሰጠው ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል፡፡
በኢፌዲሪ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ ቀሪ የ18 ወራት የጡረታ አበል እንዲከፈል ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና ከፌደራል መንግስት በመነጋገር ላይ መሆኑ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply