#የጡንቻ ህመም (muscle pain)በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ማለት ይቻላል የጡንቻ ህብረ ህዋስ ስላለ የጡንቻ ህመም በማንኛውም ቦታ ሊሰማን እንደሚችል ይነገራል፡፡ድንገት ሰውነት ሽምቅቅ…

#የጡንቻ ህመም (muscle pain)

በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ማለት ይቻላል የጡንቻ ህብረ ህዋስ ስላለ የጡንቻ ህመም በማንኛውም ቦታ ሊሰማን እንደሚችል ይነገራል፡፡
ድንገት ሰውነት ሽምቅቅ የሚያደርግ ስሜት ወይም ጡንቻዎቻችን አካባቢ የህመም ስሜት አስተውለን እናውቅ ይሆናል፡፡

የጡንቻ ህመም በጣም የተለመደ መሆኑንም ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡
ይህ ችግር በብዙ ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችልም ይናገራሉ፡፡
በዚህ ጉዳይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የሩማቶሎጂ ሰብ ስፔሻሊስት ከሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ደመላሽ ጋር ጣቢችን ቆይታ አድርጓል፡፡

#የጡንቻ ህመም #ምንድን ነው ?

ጡንቻ ላይ በሚከሰት /በሚደርስ ብግነት የሚመጡት ከኢንፌክሽን እና ከኢሚውኒቲ መስተጋብር ሊመጡ ይችላሉ ይላሉ ባለሙያው፡፡

#መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

– የሰውነት ድባቴ ውስጥ መግባት
– የነርቭ ስርአት መፋለስ ችግር
– የሚወሰዱ መድሃኒቶች
– “Acute febrile illness ” ይጠቀሱበታል፡፡
ሌላው ምክንያቱ የማይታወቅ የጡንቻ ህመም መኖሩንም ነግረውናል፡፡

#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው ?

– የሰውነት ቁስለት መሰማት
– ሰውነታቸውን ሲነኩ የህመም ስሜት መፍጠር
– ሀሳብ መሰብሰብ መቸገር
– የስሜት መለዋወጥ
– ድካም መሰማት ይጠቀሱበታል፡፡

#በምን ምክንያት ሊባባስ ይችላል?

– የስራ ጫና በሚበዛበት ግዜ
– ሴቶች የወር አበባ በሚመጣበት ሰአት
– እንቅስቃሴ በምናበዛበት ሰአት
– የእንቅልፍ እጦት በሚኖር ሰአት

#መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው ?

– ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
– ማሳጅ ማድረግ
– ፊዚዮቴራፒ መስራት
– ፍልውሀ መሄድ እንደሚረዳ አንስተዋል፡፡

#ህምክናዎቹ ምንድን ናቸው ?

– የጡንቻ ምርመራ
– የደም ምርመራ
– ህመሙን እንዲቆጣጠርላቸው የሚረዱ መድሃኒቶችን መስጠት
– የበሽታውን ስም ጽፎ መስጠት ስለበሽታ እንዲውቁ ስለሚረዳምይህንን ማድረግ ይጠቅማል ይላሉ ባለሙያው።

በመጨረሻም ሁሉም ሰዉ ወደ ህክምና ተቋም ከመምጣጡ በፊት የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ዋና ነገር የሚታይ እና የሰውነት ክብደቱን መቆጣጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርአት እና የስራ አካባቢያችንን ሰላማዊ ማድረግ ህመሙን ለመከላከል ጠቃሚ መሆኑን ዶ/ር ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡

#በሐመረ ፍሬው

ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply