የጣና ሃይቅ እንቦጭ ሳይታረም አራት ወር በመቆጠሩ አረሙ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል ተባለ፡፡የጣና ሃይቅ እና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ፋሲል ድልነሳ እንቦጩ በየዓመቱ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/QNJ4B8jEsH_2d7g3H7EkUD8h1F6FLSbMyJrjosTtK8STdS_tFVmoms-o7201t9yCtWLx7hONpBE0oHmo05-UTt0lrQ7Ifw690lT-NvdI5xdLAcjWXHiAOApWXGPcuoi-Ocd3s9E91Akd-CvrZWaozbZg40y66CMmyFCKaFOEvKtE37zL7tMQHg5rYb8njR-gLj9YJt-6BAU4AF0VBD7fwABo9DWnly2wRf1tGJGJZzjybNoSjGscSo9_7_4cpPgBW56oPB6rKcMDqgPPevFWSpoRjfJWHx9nHzCegSGfHoUWJq_CL5pQ6mCLyz4yPbBt8_7BpNWP8On0uJVy1fN9cQ.jpg

የጣና ሃይቅ እንቦጭ ሳይታረም አራት ወር በመቆጠሩ አረሙ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል ተባለ፡፡

የጣና ሃይቅ እና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ፋሲል ድልነሳ እንቦጩ በየዓመቱ ክረምቱ ሲወጣ መታረም የነበረበት አረም በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት አረሙ መታረም ከነበረበት ጊዜ በአራት ወር መዘግየቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

አረሙ ተንሳፎ እንዳለ ማረም እንደነበረበት የሚገልፁት ሀላፊው ያለው የፀጥታ ሁኔታ ግን ይህንን እንዳይሰሩ እንዳላስቻላቸው ገልፀዋል።

ኤጄንሲዉ በሠላም ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ ለመስራት ባለመቻሉ በተለያየ ዘዴ አረሙን ለማስወገድ ተጀምረው የነበሩ ጥረቶች ሁሉ በክትትል መጓደል አረሙ እንደገና ወደ ከፋ ስጋትነት መመለሱ ተነግሯል፡፡

የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በአማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የሠላም እጦት ምክንያት የህዳሴ ግድቡ መጋቢና የከተማው እስትንፋስ የሆነው ጣና ሃይቅ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሃይቁን ከዚህ ተግዳሮት ለመታደግ የሚደረገው ጥረት በየጊዜው በክልሉ የሚፈጠሩ የሠላም ችግሮች እየተደናቀፈ ይገኛል ብሏል ቢሮዉ በመግለጫዉ፡፡ ቀደም ሲል በመንግስት ግዥና በተለያዩ ድጋፎች የመጡት የአረም ማስወገጃ መሳሪያዎች አፈር እየበላቸውና ተበላሽተው ከጥቅም ውጭ እየሆኑ እንደሆነ ቢሮው ገልጿል።

በለአለም አሰፋ

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply