You are currently viewing የጣይቱ ትምህርት እና ባህል ማእከል ወደ አገልግሎቱ ሊመለስ ነው፡፡

የጣይቱ ትምህርት እና ባህል ማእከል ወደ አገልግሎቱ ሊመለስ ነው፡፡

የጣይቱ ትምህርት እና ባህል ማእከል ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተረክቦት የነበረዉን 120 አመት ያስቆጠረን የቅርስ ቤት የእድሳት ስራ 95% ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ዉስጥ የሚገኘዉ የቢትወደድ ሀይለጊርጊስ ወ/ሚካኤል መኖሪያ ቤት የነበረዉ እና የመጀመሪያ ማዘጋጃ ቤት በመሆን ያገለገለው ጥንታዊ ቤት እድሳት 95 በመቶ የሚሆነዉን ስራ ማጠናቀቁን ማእከሉ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልፆል።

ከፍተኛ የቅርፅ ባለሙያዎች ጥናት እና ከቦታዉ ጋር የሚመጥን የማስፋፊያ ዲዛይን ተደርጎበታል የተባለው ባህል ማእከልን ለማጠናቀቅ ሁለት አመት እንደፈጀ ለማወቅ ተችሏል።

ምንም አይነት እድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ የእድሳት ሂደቱን አስቸጋሪ አድርጎታል የተባለ ሲሆን የቅርስ ይዘቱን ሳይለቅ ለማደስ ሲባል የጥሬ እቃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር ግንባታዉን የመሩት አቶ ተስፋዬ አዶላ ለኢትዩ ኤፍኤም ገልፀዋል።

በአርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ሀሳብ አመንጪነት ቦታዉን ወደ ባህል ማእከልነት ለመቀየር በማሰብ በ 2011 ዓ.ም ከ/ከተማ መስተዳድር ቦታዉን መረከቡ የሚታወስ ነዉ፡፡

ቀሪ ለማእከሉ የሚያስፈልጉ የመብራት ገጠማ እና ሌሎች ስራዎችን በመጨረስ በቅርብ ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ እና ለከተማውም አማራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆን ተጠብቋል።

በቁምነገር አየለ

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply