የጤና ሚኒስቴር እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር  በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የጤና ሚኒስቴር እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ስለሚሰሯዋቸው ስራዎች መከሩ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፥የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና የሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራሮች በተገኙበት የምክክር መድኩ ተካሂዷል።

በምክክሩ በቀጣይ በሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶች በጋራ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት በተመረጡ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀናጅቶ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።

በተለይ የጤና ዘርፍ የሰው ሀብት ልማትን ላይ በጋራ ለመስራ ከስምምነት ተደርሷል።

የጤና ትምህርት ስልጠና ጥራት፤ የከፍተኛ ትምህርት እውቅናና የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስርዓት፣የጤና ዘርፍ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ማትጊያ ስርዓቶች ፣የዩንቨርሲቲ ሆስፒታሎች አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራሞች አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የተለዩ ማነቆዎችን በትኩረት ለመፍታትም መክረዋል።

የሁለቱ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የጋራ ኮሚቴ በየወሩ እየተገናኘ በስትራቴጂክ ጉዳዮች አቅጣጫ በመስጠት ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚሰራ መሆኑን ሚንስትሮቹ በጋራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የጤና ሚኒስቴር እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply