የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ጎበኙ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በደሴ ሪፌራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ በህግ ማስከበር ዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸው የሰራዊት አባላትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ ከዶክተር ሊያ በተጨማሪ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው እና የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜጀር ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በደሴ ሪፌራል ሆስፒታል ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የስራ ኃላፊዎቹ ጉዳት የደረሰባቸው የሰራዊቱ አባላት ለሀገራቸው  እና ለህዝባቸው ለከፈሉት ዋጋ ትልቅ ክብር እንዳላቸው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በትናንትናው ዕለት በቆቦ፣ በወልዲያ እና በመርሳ ሆስፒታሎች የሚገኙ ቁስለኞችን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply