የጤና ዘማቾች ለአቅመ ደካሞች

https://gdb.voanews.com/01a10000-0aff-0242-2d87-08da8212a004_tv_w800_h450.jpg

ከመቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞችና ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት የሚሠጡ ባለሙያዎችን በመላ አገሪቱ ሊያሠማራ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው ከስፔሊስት ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ባሉ በጎ ፈቃደኛ ሃኪሞች መሆኑን የጤና ሚኒሰትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

አገልግሎቱ በጤና ተቋማትና ጊዜያዊ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ሊያ ጠንከር ያለ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ወደ መንግሥት ሆስፒታሎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply