የጤፍ ምርት ለዓለም ገበያ ሊቀርብ ይገባል ሲሉ የጎጃም አርሶ አደሮች ጠየቁ። ባህርዳር:- መጋቢት 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከማዳበሪያ አቅርቦት እና የኑሮ ው…

የጤፍ ምርት ለዓለም ገበያ ሊቀርብ ይገባል ሲሉ የጎጃም አርሶ አደሮች ጠየቁ። ባህርዳር:- መጋቢት 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከማዳበሪያ አቅርቦት እና የኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ባህርዳር ድረስ ዘልቀው ቅሬታቸውን ለክልሉ መንግስት አቅርበዋል። ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች የተወጣጡ አርሶ አደሮች የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ከከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ጋር ትናንት ተወያይተዋል። የማዳበሪያ ዋጋ ንረት፣ የአቅርቦት እጥረትና ችግሩን በሚያባብሱ አካላት ላይ እርምጃ ከመውሰድ አኳያ መንግስት ተገቢ ትኩረት እንዳልተሰጠ በውይይታቸው አንስተዋል። በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የኢንዱስትሪ ውጤት የሆኑትን ቆርቆሮ፣ሳሙና፣ዘይት፣ ባትሪ ድንጋይ እና የመሳሰሉ ሸቀጦችን መግዛት አለመቻላቸውንም በቅሬታቸው አንስተዋል። የትግራይ ወራሪ ኃይል በክልሉና በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን የግፋ ወረራ ለመቀልበስ ልጆቻችንን መርቀን ወደ ጦር ግምባር ከመላክ ባሻገር በግል የጦር መሳሪያና ስንቃችን ተፍልመናል ሲሉ አርሶ አደሮቹ አውስተዋል። አሁንም ዳግም ወረራውን ለመመከት ተዘጋጅተን ባለንበት ሁኔታ ላይ ለተጠቀሱ ችግሮች አፋጣኝ መፋተሄ ማስቀመጥ የመንግስት ግዴታ ነው ሲሉም በአፅንኦት ገልጠዋል። ቦቆሎን ጨምሮ ምርጥ ዘር ነው እያሉ ልዩ ልዩ የሰብል ዝርያዎችን በማሸግ በሚያጭበረብሩ ህሌና ቢሶች እና የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ሸቀጣሸቀጦችን በመከዘን ችግሩን በሚያባብሱት ላይ መንግስት ተገቢ እርምጃ አለመወሰዱንም ተችተዋል። የችግሩ ምንጭ ” ከቢሮ እስከ ጓሮ ” ያሉ ትቂት ስግብግብ አካላት ሆነው ሳለ ፈጣንና ተመጣጣኝ እርምጃ አለመውሰድ ካሁኑ መጭውን የሚያከብድ ቸልተኝነት ነው ሲሉ አሳስበዋል። ሁሉንም ችግሮች ከውጭ ምንዛሬ ጋር ማያያዝ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮቦስት) ተጠቀሙ ብሎ መምከር ላሁን ችግራችን መፋተሄ አይሆንምም ብለዋል። ለዘላቂ መፋተሄ ከጤፍ ምርታችን ከልፋታችን ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ተጠቃሚነታችንም እንዲረጋገጥ ጤፍ ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ መንግስት አልሞ ይስራልን ሲሉ ጠይቀዋል። በየደረጃው ካሉ የመንግስት አካላት መልካም አገልግሎት ባናገኝም ክቡር ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በሰጡት አቅጣጫ በዚህ ሁኔታ መወያዪት በመቻላችን ለመሪያችን አክብሮትና ምስጋና አለንም ብለዋል አርሶ አደሮቹ። መንግስት ” ከልማትም ቀለብ ይቅደም ” በሚል መርህ ለአንገብጋቢ ቅድሚያ ትኩረት ለሚሹ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ታሳቢ አድርጎ ይስራልን ሲሉ መክረዋል። ከአርሶ አደሮቹ ጋር ውይይት ያካሄዱት የርዕሰ መስተዳደሩ የኢኮኖሚ ጉዳይ አማካሪ አቶ አስናቀ ይርጉ እና የርዕሰ መስተዳደሩ ልዩ ረዳት አቶ ደሳለኝ አስራደ ናቸው። አቶ አስናቀ እንዳሉት በአርሶ አደሮቹ የቀረቡ ጥያቄዎች፣ትችትና ምክረ-ሀሳቦች ተቀባይነት አላቸው ። አቶ ደሳለኝ አስራደ በበኩላቸው መሰል ችግሮችን አዳምጦ በሀቅ ላይ የተመሰረተ ምላሽ መስጠት የመንግስት ግዴታ ነው ብለዋል። የጤፍ ምርት ለዓለም ገበያ ይቅረብ፣ ችግሩን በሚያባብሱ ህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰድ የተባለውን የአርሶ አደሮች ሀሳብ መንግስትም ይጋራል ብለዋል። የመፍትሄ እርምጃዎችን ለመውሰድም የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። የገጠመን ችግር ውስብስብ መሆኑን ተረዱን ያሉት አቶ ደሳለኝ መፍተሄም ከመንግስት ብቻ የሚጠበቅ እንዳልሆነ ማሳያዎችን በመጥቀስ አስገንዝበዋል። በጋራ እየመከርን የእናንተን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ይዘን ችግሮችን ለመሻገር አምረን በመታገል የአፈር ማዳበሪያ ጉዳይን ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሲሉ አቶ ደሳለኝ አስታውቀዋል። #የኔታ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply