የጥርን በባህር ዳር መርሃ ግብር አካል የሆነው ዓመታዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲ…

የጥርን በባህር ዳር መርሃ ግብር አካል የሆነው ዓመታዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የጥርን በባህር ዳር መርሃ ግብር አካል የሆነው ዓመታዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ (የሰባሩ ጊዮርጊስ) በዓል በእለተ ቀኑ ጥር 18/2015 በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። በዓሉ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን፣ የባህር ዳር እና የአካባቢውን አማራዊ ወግ እና ባህል በጠበቀ መልኩ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት መከበሩን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ከመንበሩ ከጠዋት ጀምሮ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአባቶች ጸሎት፣ በከፍተኛ እልልታ፣ ጭብጨባ፣ ጭፈራ ጭምር ታጅቦ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላም ጣናን ተንተርሶ በአዲስ እየተሰራ ወደሚገኘው ጥምቀተ ባህር ተወስዶ አርፍዷል። ከሰዓት በኋላም ታቦቱ ወደ መንበሩ እንዲመለስም ተደርጓል። በዓሉም በሀይማኖታዊ እና በባህላዊ አልባሳት ባጌጡ እና በተዋቡ፣ በሰንደቅ አላማ ባሸበረቁ የሀይማኖት አባቶች፣ በባህር ዳር እና አካባቢው በሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች እና በአጠቃላይ በበዓሉ ተሳታፊዎች ተከብሮ ነው የዋለው። በተለይም የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እና አዝማሪዎች ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ሰጥተውት እንደዋሉ አሚማ ተመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply