የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡ በዛሬው ዕለት የተመረቀው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተለያዩ የሕክምና ግብዓቶች እንደተሟሉለት ተነግሯል። ለአብነትም በአፍሪካ ብቸኛው ልብ ሳይከፈት ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ተበርክቶለታል ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ለፕሮጀክቱ 39 ነጥብ 720 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ወጪውም 50 በመቶው በኔዘርላንድስ መንግሥት ቀሪው ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላትና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply