የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረከበ፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ሠራዊቱ የፈፀመው ተግባር መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያኮራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ሠራዊቱ ላከናወነው የጀግንነት ተግባር ያደረግነው ድጋፍ ያንሰዋል” ብለዋል።

በሰራዊቱ ላይ በህወሃት ጁንታ የተፈጸመው የክህደት ጥቃት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት በእጅጉ ያስቆጣቸው እንደነበርም አስታውሰዋል።

ክህደት የተፈጸመበት ሰራዊት ራሱን አደራጅቶ የህግ ማስከበር ዘመቻውን አጠናቆ ወንጀለኞችን ወደ ማደን ተግባር መግባቱ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸው፤ “የወደፊት ልጆቻችን ይማሩበታል” ብለዋል።

ማህበሩ ካለው ላይ ቀንሶ ድጋፍ ማድረጉ ለሠራዊቱ ያለውን ክብር ለማሳየት መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዘንድሮ የሚከበረውን 80ኛውን የድል በዓልን ከሠራዊቱ ድል ጋር በማያያዝ በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ ሰራዊቱ አብሮ እንዲያከብር ጥሪ አድርገዋል።

ድጋፉን ተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ማህበሩ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ላሳየው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የሕግ ማስከበር ዘመቻው የመከላከያ ሠራዊቱ የአባቶቹንና የአያቶቹን ጀግንነት የደገመበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply