የጥፋት ቡድኑ በመንዝ ጌራ ምድር የገጠር ቀበሌዎችና በመሐል ሜዳ ከተማ የልማት መሰረተ የሆኑትንና ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን አውድሟል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 9 ቀን 20…

የጥፋት ቡድኑ በመንዝ ጌራ ምድር የገጠር ቀበሌዎችና በመሐል ሜዳ ከተማ የልማት መሰረተ የሆኑትንና ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን አውድሟል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግራይ የጥፋት ቡድን በሰሜን ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር የገጠር ቀበሌዎችና በመሃል ሜዳ ከተማ በቆየባቸው 12 ቀናት በርካታ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡና የመሰረተ ልማት ተቋማትን ማቃጠሉንና መዝረፉን የተቋማት ኃላፊዎችና ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ቡድኑ ካቃጠላቸው ተቋማት ውስጥም በመሃል ሜዳ ከተማ የሚገኘውን የኢት ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከል፣ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤትና የመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 6 ፅህፈት ቤቶችን ሰለባ እንዳይኖራቸው በማድረግ አውድሟል፡፡ ከዚህ ባለፈም ይህ በጥፋት የተጠመደው ቡድን የመሐል ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታልን፣ መሰናዶ ትምህርት ቤትና ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በመዝረፍ፣ ቀሪዎቹንም እንዳያገለግሉ በመሰባበርና በማጉደል ማውደማቸውን የተቋማቶች ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡ አብርሃም ሸንቁጤ የመንዝ ጌራ ምድር ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው ድህነት ተኮር የሆነውን 14 ክፍሎች ያሉት ተቋም ዘራፊው የትግራይ ኃይል በእሳት አቃጥሎታል፤ ሌሎች ተቋማትንም ዘርፋል፡፡ ይህ ግብርና ተቋም ብቻ ከነመገልገያ እቃዎቹ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት አጥፍቷል ብለዋል፡፡ በተያያዘም የመሐል ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ወርቅነህ ዘውዴ እንደገለፁት፤ የጥፋት ቡድኑ በሆስፒታሉ ያገኛቸውን መድሃኒቶች በመዝረፍ፣ ቀሪዎቹን ጥቅም እንዳይሰጡ በማድረግ፣ ህንፃውን በከባድ መሳሪያ ጭምር በመሰባበርና ውድ የሚባሉ የህክምና እቃዎቹን ከመውሰድ እስከ ማውደም ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ ለጊዜው ባለው ነገር ህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውንም ነግረውናል፡፡ በተመሳሳይ በመንዝ ጌራ ምድር ፀሐይ ሲና ቀበሌ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የህክምና ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች ፣በጥፋት ቡድኑ መውደሙንና መዘረፉን እንዲሁም የቀበሌው ግብርና ጽህፈት ቤት የእንስሳት መድሃኒቶች መዘረፉን ቀበሌው ሊቀ መንበር አቶ አሳልፍ ወርቁ ገልጸውልናል። በአጠቃላይ የቀበሌው ሙሉ ንብረት መዘረፉን ተናግረዋል ሲል የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ገልጧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply