You are currently viewing “የጦርነቱ,ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአፋር እና የአማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት መሆን እንደሚገባቸው አጽንዖት በመስጠት እናሳስባለን።”      እናት ፓርቲ አማራ…

“የጦርነቱ,ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአፋር እና የአማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት መሆን እንደሚገባቸው አጽንዖት በመስጠት እናሳስባለን።” እናት ፓርቲ አማራ…

“የጦርነቱ,ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአፋር እና የአማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት መሆን እንደሚገባቸው አጽንዖት በመስጠት እናሳስባለን።” እናት ፓርቲ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ኹለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ካጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ኹሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው፡፡ ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዟችንን ለብዙ አሥርት ዓመታት ወደኋላ መልሷልና! ፓርቲያችን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽመግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አኹንም ያ ውድመትና ውረድ እንውረድ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት ፓርቲያችን በደስታ የሚመለከተው ኩነት ነው፡፡ በእርግጥ ብንታደል በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው፤ ከተከሰተም በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ በውደድን፡፡ ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው፡፡ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን “አላስፈላጊ” ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ “ጅብ ፈርቸ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ በማዕከላዊ መንግስት በኩል ከአኹኑ የአካሄድ መጣረስ /Procedural fallacy/ እየታየ ነው፡፡ አዎ፣ ችግሩን የፈጠረው የሕወሓትና ብልጽግና የስልጣን ሽኩቻ ነው፤ የተዋጋውና ዳፋው የተረፈው ግን ሕዝብና መንግስት በመሆኑ ወደአንድ ፓርቲ ለመጎተት የሚደረገው ጥረት አዋጭ እንዳልሆነ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡ ወዲህም ፓርላማው ሕወሓትን አሸባሪ በሚል ፈርጇል፡፡ ምንም እንኳን እንዳለመታደል ሆኖ የአንድ ፓርቲ ውቅርም ቢሆን ድርድሩን መፍቀድ፣ ከሽብርተኝነት መሰረዝ፣ የድርድር ነጥቦችን ማውጣት፣ ብቁና ወካይ ተደራዳሪዎችን መሰየም፣ ሂደቱን በየጊዜው መከታተል፣ ውጤቱንም ማጽደቅ ያለበት ፓርላማው ሆኖ ሳለ የፓርቲ ውሳኔ እንደመንግስት ውሳኔ ተቆጥሮ ዘሎ የማለፍ አዝማሚያ አደገኛ ውጤት ያለው ነው ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም ፓርቲያችን ለድርድሩ ውጤታማነት ቀጥሎ ያሉ ነጥቦችን ከግንዛቤ እንዲገቡ ያሳስባል፡፡ ፩. በፌዴራል መንግሥት ከሚወከሉት በተጨማሪ የጦርነቱ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአፋር እና የአማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት መሆን እንደሚገባቸው አጽንዖት በመስጠት እናሳስባለን። በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ሕዝብንም ስሜት በትክክል የሚያንጸባርቁ አካላት እንዲወክሉት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ፪. የእኛን የኢትዮጵውያንን ችግር ከእኛ የተሻለ ማንም የሚረዳው እንደማይኖር በመገንዘብ በገለልተኛ አካላት (ሲቪክ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ምሁራን) አማካኝነት ተደራዳሪዎች በሚስማሙበት ቦታ እንዲካሄድ፤ ይህ ካልሆነ ድርድሩ በአፍሪካ ኅብረት አመካኝነት እንዲካሄድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ፫. አጠቃላይ ድርድሩ እንደመንግስት እንዲመራና ፓርላማው ሙሉ ሂደቱን እንዲመራው፤ ውጤቱም ተግባራዊ የሚሆነው በፓርላማው ሲጸድቅ ብቻ እንዲሆን፤ ተደራዳሪዎችም የአንድ ፓርቲ ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ በእውቀታቸው፣ ልምዳቸው፣ በሀገራቸው ጥቅምና ሉዓላዊነት የማይደራደሩና የፓርቲ ውክልና የሌላቸው አካላት ጭምር እንዲካተቱበት አበክረን እንጠቃይለን፡፡ ፬. ለድርድሩ ስኬታማነት ከመንግስት ጥረት ጎን ለጎን ሕዝብ፣ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃን አዎንታዊ አስተዋጽዖ በማድረግ በተለይ ከኹለቱም ወገን አላስፈላጊ የአደባባይና የውስጥ እንካ ስላንትያዎች እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላለፍለን፡፡ ፭. ድርድሩሕዝብን የሚያቀራርብ፣ ቂምና ቁርሾን የሚሽር፣ ግልጽና ጥፋተኛን በውል የሚቀጣ፣ ከሴራና እልኸኝነት የራቀ ለሕዝብ በየጊዜው ይፋ የሚደረግ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡ ፮. በአጠቃላይ ወደ ድርድር የምንገባው ከጦርነት ተላቀን እንደሀገር ብዙ ለማትረፍ እንጂ ለበለጠ ኪሣራ አይደለምና ሂደቱ የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት በምንም መልኩ ለድርድር የማያቀርብ እንዲሆን አበክረን እናሳስባለን፡፡ በመጨረሻም ድርድርና እርቅ የሚወደድ ተግባር ነው፡፡ የምንደራደረው ግን ከ“ሕወሓት” ጋር በመሆኑ የጸጥታ ኃይሉ ከመዘናጋት ይልቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ በመናበብ፣ ከፍ ባለ ዝግጅት እና በተጠንቀቅ እንዲቆም አበክረን ማሳሰብ እንወዳለን፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply