የጨረታ መክፈቻው መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስታወቀ።የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3,452 የመኖ…

የጨረታ መክፈቻው መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ ከሕብረተሰቡ መጣልኝ ባለው ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ አሳውቋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply