የጨቅላ ህፃናትን አስክሬን እንሰት ስር ቀብራ የተገኘችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡ በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዉብ አሪ ወረዳ አይዳማሪ ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ግለሰብ፣…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/viIuGXhayCwkvHIBoJXTMFSVefavmW4XNlY5nckD6TymwgwTJBKE3ztqny8X8-myFD27NF6Vv6c1s6_qmcvZuQClnZ95OicFcW97goAJKbBfKyWtrEasy1zIzTMx5cDLy7aA-i2oWPlsKiawACAMZimHq9I_Hew9qLNFvM5Zu7ZMXAVlqQRQUyom7W-98OR-IGrohxNiTdE-inHEfDV7Eoa8NQqg0GFZg6p3cWcPvyCHK4zDR5qdBfhkwlKw-5-SUrID9AwJqoBXOtIPTDc9nsmRS3cvsiHF-KW-3L5eTkb07hwpA_hfM17Apwbm4Xgfp6qrII-SByWilYR_Pbo7hQ.jpg

የጨቅላ ህፃናትን አስክሬን እንሰት ስር ቀብራ የተገኘችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዉብ አሪ ወረዳ አይዳማሪ ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ግለሰብ፣ ከአራት ጊዜ በላይ እናቶችን እያዋለደች የህፃናት አስክሬን ከቤቷ ጓሮ እንሰት ስር ቀብራ በመገኘትዋ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተነግሯል፡፡

የልምድ አዋላጅ ነኝ በማለት ነፍሰጡር እናቶች ወደ ጤና ጣቢያ ሄደዉ በህክምና ሙያተኞች የወሊድ ድጋፍ አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ ማድረጓን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ተናግረዋል።

ምጥ የያዛቸዉ እናቶችን ስታዋልድ የፅንሱ ህይወት ሲጠፋባት በራሷ መኖሪያ ቤቷ ጓሮ መቅበሯን ፖሊስ ከህብረተሰቡ በተሰጠው ጥቆማ መነሻ በተጠርጣሪዋ ላይ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል።

ፖሊስ ከጤና ጽህፈት ቤትና ከሴቶችና ህፃናት ጋር በጋራ በመሆን ባደረገዉ ማጣራት የአራት ህፃናት በድን አስክሬን ከተጠርጣሪዋ ጓሮ እንሰት ስር ተቀብሮ መገኘቱ ተረጋግጧል።

ተጠርጣሪዋ ከፈፀመችዉ የመጀመሪያ ስህተት መማር ሲገባት ከአንዴም አልፎ ለአራት ጊዜ ያህል ተመሳሳይና ተደጋጋሚ ስህተት ሰርታ በመገኘትዋ ልትቀጣ እንደቻለች ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ገልጸዋል፡፡

መረጃው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply