የጸሎትን ብትር ማንም አይመልሰው! – ምሕረት ዘገዬ

ዘመናችን በጥቅሉ የጭንቀትና የጥበት መሆኑ ከዓለም አቀፍ አስከፊና አሳዛኝ ክስተቶች በመነሳት በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ የኛ ግን ከሁሉም የባሰ ነው፡፡ ሕንጻ በቦምብ ናዳ ስላልፈረሰ ብቻ ሀገር አማን ነው አይባልም፤ ሰው በመንፈስና በአካል እየፈረሰ ነውና፡፡

ጭራሹን ማሰብ የተሳነው የሕወሓት መንግሥት የሚሠራውን አጥቶ በዕብደት ጎዳና እየተመመ ነው፡፡  ወያኔዎች ተስፋ በመቁረጣቸው ሳይሆን አይቀርም የሚሠሩት የክፋት ሥራ ሁሉ ቅጥአምባሩ ጠፍቷል፤ በዓለም ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ዕኩይ ተግባራቸው የዞረ ድምር ያለው መሆኑን በፍጹም ዘንግተዋል፡፡ የጥጋብ  ሞራ ኅሊናቸውን ስለሸፈነው፣ የቂመኝነት አባዜ ልባቸውን ስለደፈነው፣ የዘረኝነት ዝልል አእምሯቸውን ስላሰከረው፣ ለትግራይና ሕዝቧ ቀርቶ ለራሳቸው ነፍስና ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው የወደፊት ዕጣም ማሰብ አልቻሉም፤ ማሸነፍ ብርቁ የሆነ ሰው ሲያሸንፍ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ትንሽ ሰው – በአስተሳሰብ ማለቴ ነው  – አያሸንፋችሁ፡፡ እነዚህ ከውሻ የማይሻሉ ወያኔዎች የኛን የኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ ድብቅ ገመናውን አጋልጠው አወጡት፡፡ እንዲህ ያለ የፈሪ ጭካኔ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡( ከውሻ አለመሻላቸው – ውሻ ሲሸነፍ ተሸናፊው በጀርባው ይተኛና ላሸናፊው ሀፍረቱን ገልጦ ያሳያዋል አሉ፡፡ ያኔ አሸናፊው ማሸነፉን ተረድቶ ማጥቃቱን ያቆማል፡፡ ወያኔ ግን የቆመን ይቅርና የሞተ በድንንና የተቀበረ ዐፅምን በእውኑም በምናቡም እየተፋለመና ራሱ በፈጠረው ጠባብ የስቃይ ዓለም ውስጥ እንዳሣማ  እየተንደባለለ የሚኖር የሰው ልጅ ማፈሪያ ፍጥረት ነው፡፡)

ዕድገትና ለውጥ በወያኔ መንደር አይታወቁም፡፡ ከሚያደርሱት ጥፋትና ውድመት አኳያ እንዲህ ማለት የሚቻል አይሆንም እንጂ ወያኔዎች እንደተወለዱ ሞቱ ቢባሉ ያስኬዳል፡፡ ሰው መቼም ሰው ነውና ከዕድሜም ሆነ ከትምህርትና ከተሞክሮ እየተማረ ሕይወቱን አስተካክሎ ይመራል፡፡ እነሱ ግን ከመነሻው አስተዳደግ በድሏቸዋልና – ብዙዎቹ የባንዳ ልጆች እንደመሆናቸው የትውልድ እርግማንም አለባቸውና – አንዴውኑ እንደተጣመሙ በጊዜ ሂደት ሊለወጡ አልቻሉም፡፡ በልጅነት የወረሳቸው የዘረኝነት ልምሻ ሳያስቀብር የሚለቃቸው አልሆነም፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በአሥራዎቹ ዕድሜውም በሰማንያዎቹም አንድ ዓይነት ስብዕና ካለው ይህ ዓይነቱ ሰው ከድንጋይ የሚያንስ ግዑዝ ፍጡር እንጂ ሰው ሊባል አይገባውም፡፡ እነአቦይ ስብሃት ነጋና አባይ ፀሐዬ እንግዲህ የጥፋት ፊታውራሪዎች የሆኑ የእንጨት ሽበቶች ናቸው፡፡ ለመሸበት ለመሸበት ድንጋይና እንጨትም ይሸብታሉና እነኚህን መሰል ዜጎች ሳይፈጠሩ እንደጨነገፉ ቢቆጠር ስህተት የለውም፡፡ ሌሎቻችን ግን ከነዚህ ውሾች መማር አለብን፡፡

የነናቡከደነፆርና የነፈርዖን አረመኔያዊ አገዛዝ ከነዚህ ወያኔዎች አገዛዝ በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡ እኚያ የጥንት ጨካኞች በእስር ቤት ያዋሉትን ሰው ከፈረዱበት ወይም በፍርድ ሂደት ካዋሉት በኋላ እየደበደቡ እንደማይገድሉት መገመት ይቻላል፡፡ እነዚህ ጉዶች ግን በህግ ጠለላ ሥር ያለን ሰው በእርግጫ ደረት ደረቱን እያሉ ይገድላሉ፡፡ ሰሞኑን በርካታ እስረኞች በዚህ መልክ እየሞቱ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ በውነቱ ወያኔዎችን ሳስብ ስም አጣላቸዋለሁ፡፡ አመክሮና ምሕረት በሌለው ሁኔታ ተከፍሎ ሊያልቅ ባልቻለው የኃጢኣታችን ውጤት ቅጣትና በጌታ የቁጣ ክምርም አምርሬ አዝናለሁ፡፡ ኧረ አሁንስ በቃችሁ ይበለን! 43 ዓመት??

የወያኔዎች ወንጀል የሚከፋው ወንጀል ይፈለስፉና ለሚጠሉት ሰው ያስታቅፋሉ፡፡ “የምትሉትን አላደረግሁም” ሲባሉ እነዚህ የሌባ ዐይነ ደረቆች ንጹሑን ሰው ያልሠራውን ወንጀል እንዲያምንና እንዲፈርምበት ያስገድዳሉ፡፡  በዚህ መልክ እስር የገባን ሰው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ወህኒ ቤት ውስጥ እያለ በእሳት አቃጥለው እንዲሞት ያደርጋሉ፡፡ እራሳቸው እሳት ለኩሰው ባቃጠሉት ወህኒ ቤት ውስጥ የገደሉትን ይገድሉና በሕይወት የተረፈውንና ከእሳት ሊያመልጥ የሚንፈራገጠውን እስረኛ  “ ከወህኒ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ” ብለው ያላግጡበታል፡፡ ሊያመልጥ ያልሞከረውንና ለጥይታቸው ሰለባ መሆን ያልፈለገውን ደግሞ በእሳት ለኳሽነት በሀሰት ክስ ላይ ሌላ የሀሰት ክስ መሥርተው ያንገላቱታል፡፡ ለክስም ለሽሽትም ያልተንበረከከውን የኅሊናና የአካል እስረኛ በእርግጫና በጥፊ በቦክስና በካልቾ እያዳፉ ለሞት ይዳርጉታል፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ናቸው፡፡ ከዚህም ባለፈ ሊነገር የማይችል ኢሞራላዊና ኢሃይማኖታዊ ሰቅጣጭ የሰይጣን ድርጊት በካቴና በታሰረ ዜጋ ላይ ይፈጽማሉ፡፡ በበደል ጽዋቸው ውስጥ እያከማቹት ያለውን የግፍ ቁልል ስናይ መቼ ከፍለው እንደሚጨርሱት ልንገምት ባለመቻላችን እንገረማለን፡፡ የፈረደበት ትውልድ ግን ከዕዳው አያመልጥም! ወዮ ለቀኑ በሉ፤ ቀኑ ሲደርስ በደረቅ አበሳ እርጥብ መቃጠሉ የማይጠበቅ ሳይሆን የታሪክ ፍርጃ ነው፡፡ ብዙ አየና!

ተጋሩ ወንድምና እህቶቼ እባካችሁን ከነዚህ የእፉኝት ልጆች ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ፈጣሪ ይህን ሁሉ “ዕድል” ለነዚህ ክፉዎች የሰጠበት አንዳች ምክንያት ቢኖረው ነው፡፡ አለነገር እነዚህ ሰዎች በዚህች ታሪካዊ ሀገር አልሰለጠኑም፡፡ የምናካክሰው ያለፈ በደልና ክፉ ሥራ ቢኖር ነው ለነዚህ የመርገምት ውሉዳን አሳልፎ የሰጠን፡፡ ራሳችንንና ታሪክን እንመርምር፡፡

በቅርብ የሰማሁትን አንድ ቀልድ መሰል እውነት ጣል ላድርግና ወደ ዋናው ጭብጥ ገብቼ ልሰናበት፡፡ ትግሬ ፌዴራሎች አንድን  ወጣት ይዘው ይቀጠቅጡታል አሉ፡፡  እየቀጠቀጡት ሳለ ወጣቱ በኪሱ ያለው የሞባይል ስልክ ይጮሃል፡፡ ቀጥቃጩ ፌዴራልም ተደብዳው ልጅ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ እንዲያናግር ቀጭን ትዛዝ ያስተላልፍለታል፡፡  በስልኩ ጩኸት ከድብደባው እፎይታ ያገኘው ወጣት ስልኩን እያወጣ ሳለ ፌዴራሉ “ለስልኩን ላውድ ላይ ግበሮ” ይለዋል፡፡ ልጁም በታዘዘው መሠረት “ላውድ” ላይ አድርጎ መቀበያ ቁልፉን ይጫናል፡፡ በወዲያኛው ጫፍ ያለው ደዋይ “ቧይ ስለምንድንው እንዴ ቶሎ እማታነሳው – ገብረ እግዚአብሔር አይደለህም እንዴ?” ሲል ያምቧርቃል፡፡ ይሄኔ ያ ወጣት “እሱን ብሆንማ በማን ዕድሌ!” ብሎ በቁጭት ይናገራል፡፡ ይታያችሁ – ኢትዮጵያን ማን ወደ እንጦርጦስ እያወረዳት እንደሆነ ልብ በሉ፡፡ ያስጠይቃል፡፡ በእግረ መንገድ – ትዝ ስላለኝ ነውና ይቺን ደግሞ ላልሰማችሁ ልመርቃችሁ፤ አንዱ ጓደኛውን “ኑሮእንዴት ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል አሉ፡፡ ሲመልስ “ከላይ እግዚአብሔር፤ ከታች ገብረ እግዚአብሔር ሳሉ ምን እሆን ብለህ?” በማለት በውስጠ ወይራ ቅኔ አዘል ብሶቱን እንደዋዛ ጣል ያደርግለታል፡፡ ብዙ ነገር አለ፤ ወደፊት ብዙ ጉድ ይወጣል፡፡

እኛ የገዛ ነፃነታችንን ለማምጣት የታደልን አንመስልም፡፡ አንድ ነን ስንል መቶ እንሆናለን፡፡ ዕንቆቅልሽ ፖለቲካ ውስጥ ገብተን እየዳከርን ነን፡፡ የተጣለብን አንደርብ እንዲህ በቀላሉ የሚለቀን አልሆነም፡፡ የተቃውሞው ጎራም እርስ በርሱ ለመራኮት የሚያውለው አጠቃላይ ሰብኣዊና ቁሣዊ በጀት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሣ አሁን ወያኔ ቢወድቅ እንኳን ለሀገር የሚያውለው አቅም የሚኖረው አይመስልም፡፡ የኢትዮጵያውያን ባሕርይ በዚህ ዘመን ክፉኛ ተለዋውጧል፡፡ መጨረሻችንን ያሳምርልን እንጂ የገባንበት አዘቅት ቀላል አይደለም፡፡ አያ ሞትም፣ አያ ዕድሜም የየበኩላቸውን ድርሻ እየሞጨለፉ ደህና ደህና ሰዎችን እያሳጡን ነው፡፡ ይህ ሞት የሚሉት ወያኔን የሚጠየፍ ጉድ የኪነ ጥበብ መንደራችንንም በየሰዓቱ እየጎበኘ ያም መንደር ባድማ ሊሆን ነው፡፡ ጉዳችን ፈላ!!

ኑሯችን ከቀን ቀን እየዘቀጠ በተለይ በዚህን ሰሞን የወያኔው ብር የመግዛት አቅም ወደ ዚምባብዌና ሶማሊያ ደረጃ እየወረደ ነው፡፡ አንድ ኩንታል ጤፍ 3 ሽህ ብርን እየረገጠ ነው – “እየረገጠ ነው” በምልባት በዚህች ቅጽበት ራሱ ከመርገጥም አልፎ ወደ ላይ ሊሽቀነጠር ይችላል፡፡ መንግሥትም ህግም በሌለበት ሁኔታ ነፍሳችን ውሎ የሚያድረው በኪነ ጥበቡና በተዓምር እንጂ በማኅረሰብኣዊ የኑባሬ ቀመር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንደኛውና ዋናው  መንግሥትና ህግ በሌለበትና ሙስና የደም ዝውውር ዋና ሞተር በሆነበት በዚህ አደገኛ ዘመን በተለይ እኛ ጭቁን ደሞዝተኞች ውለን ማደራችን ነው፡፡ የኢኮኖሚው መላሸቅ፣ የህግና የሥርዓት መጥፋት፣ የሞራልና የባህል መበረዝ … የዘመናችን መታወቂያ እንደመሆናው ዜጎች ከቤት ወጥተው ቢያንስ ብዙዎቹ ወደ ቤታቸው – ቤት ያላቸው ማለቴ ነው – መግባታቸው አንዳች መለኮታዊ ጥበቃ ያለን መሆኑን ብናምን ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አልተሳሳትንም፡፡ በተረፈ አያድርግብህ እንጂ መሀል አዲስ አበባ ላይ አንድ ጥጋበኛ በጥይትም ይሁን በእርግጫ ደፍቶህ ቢሄድ ጠያቂ የለውም –  ጠያቂ ኖሮ የደፋህ ሰው ቢታሰር ገንዘብ ወይም ሰው ካለው በሰዓታት ውስጥ ተፈትቶ እንደልቡ ሲፏልል ልታየው ትችላለህ፡፡ ቤትህን ወይ ንብረትህን ካስፈለገም ሚስትህንና ሴት ልጅህን ወያኔ ከፈለገ ዐዋጅ ማርቀቅና በነጋሪት ጋዜጣ ማውጣት ሳያሻው በፌዴራል ተብዬውና በአጋዚ ወታደር ገቢ ሊያደርግህ ሕወሓታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም ታሪክ መዝግቦ ይዞታል፡፡ እነዚህ ቅሌታም ወያኔዎች ያላስመዘገቡት የገማ ታሪክ የለም፡፡ ለነፃነት ቀን ያድርሰንና በገሃድ እናወራዋለን፡፤፡፡

ወደ ዋናው መልእክቴ ገባሁ፡፡ በውጭም በሀገርም ውስጥ ያላችሁ ክርስቲያኖችም ሆናችሁ ሙስሊሞች ከልባችሁ ሆናችሁ ወደየምታመልኩበት አምላካችሁ ጸልዩ – እንጸልይ፡፡ በላ እየመጣብን ነው፡፡ ይህን በላ ሊመክትልን የሚችለው፣ ይህን መቅሰፍት ሊያበርድልን  ሥልጣን ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ እንደሰው ምኞትና መፍጨርጨር ቢሆን ኖሮ ብዙዎች ለዚህች ሀገር ደማቸውን አፍስሰውና ምትክ የሌለውን ቤተሰባቸውን የትም በትነው ትልቁን መስዋዕትነት በመክፈል ወደ መቃብርና ወደ ዘብጥያ ወርደው ነበር፡፡ ግን ያለ ፈጣሪ ፈቃድ የሚሆን ነገር የለምና ነገራችን ሁሉ የእምቧይ ካብ እየሆነ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገርን እንገኛለን – በብርሃን ፍጥነት፡፡

“የጨው ተራራ ሲናድ፣ ሞኝ ይስቅ ብልኅ ያለቅስ” ይባላል፡፡ እየታዘብነው የምንገኘው ጉዳይ ይህን ይመስላል፡፡ ሀገር በጠራራ ፀሐይ እየወደመች ሳለ ዜጎች በፀጥታ ማለፍን መርጠዋል – “ተው እንዳታስጨርሰን፤ ጅቡ እየበላ ያለው የኔን እግር ነው!” ብሎ እንደተናገረው በአንድ ክፍል ያደሩ ፈሪዎች ታሪክ ሆኗል የኛም ሁኔታ – ወያኔ አማረን ገድሎ አበቅየለሽን ወይም ደቻሳን ገድሎ ጫልቱን ሊተው፡፡

ኢትዮጵያ አሁን በሕይወት ያለች የሚመስላቸው የዋሃንም በርካታ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ሕይወት ውትር ውትር ስላለች ሀገር ሰላም የሚመስላቸው ገራገሮች ሞልተዋል፡፡ ግን ግን ሁኔታውን በጥሞና ላጤነ “የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል” እንዲሉ ነው፡፡ ሩዋንዳና ሦርያ፣ ሊቢያና ኢራቅ ወደ ኢትዮጵያ እምብርት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ላይ እያሉ በሰላም ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ካለ ጅል ነው፡፡ “እኔም በአንድ ቀን አልተቆረጥኩም” ብላታለች አሉ እጇን ማሳከክ እንደጀመራት ሕጻን ልጇ የነገረቻት አንዲት የሌፕረሲ አካል ጉዳተኛ፡፡ የኛም ነገር እንደዚሁ ነው፡፡ የወያኔዎችና ጌቶቻቸው ፍላጎት ይሄውና ይሄው ብቻ ቢሆንም ፈጣሪ ግን የእስካሁኑን ቆጥሮልን እንዲምረን መጸለይ አለብን፡፡ ብርቱ ጸሎት እናድርግ፡፡ ሰይጣኑ ሙሉ በሙሉ ከጠርሙሱ ከወጣ አንችለውም፡፡ የወያኔው ጌቶች በሰዓታት ውስጥ ዜጎቻቸውን ከኢትዮጵያ በተለይም ከመናገሻዋ ከሸገር ሊያወጡ ይችላሉ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞችና የንግድ እንዲሁም የፖለቲካ ተቋማትን በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር የተቆጣጠሩት የወያኔ ጭፍሮች ግን ማንም ወደየትም አይወስዳቸውም – በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው ትግሬ ደግሞ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ከትግራይ ውጭ ባለው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፤ ጥቂት የማይባሉ ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ ትግሬዎች ቢኖሩም ተሰሚነት የላቸውም፤ የጉዳቱ ሰለባም ናቸው፡፡ በተረፈ አዲስ አበባ መቀሌን ከመሰለች ውላ አድራለች፤ አሮጌውና አዲሱ ቦሌም ሂድ – ጉለሌም ሂድ – መገናኛም ሂድ – ሰሚትም ሂድ – አያትም ሂድ – ጎሮም ሂድ – የትም ግባ ከየትም ውጣ በአዲስ አበባ የሕዝብ አሰፋፈር እጅግ ጎልቶ የሚታየው ትግሬ ብቻ ነው፤ በግርድፍ ግምት ከ80 በመቶው በላይ የአዲስ አበባ ታላላቅ ሕንጻዎችና የንግድ ማዕከላት ባለቤቶችና ዋነኛ ተጠቃሚዎች ትግሬዎች ናቸው፡፡ አማሮችና ሌሎች ዜጎች ሀብት ማፍራት ቀርቶ በሕይወት መኖር አይፈቀድላቸውም፡፡ ለአንድ አማራ ዘመናዊ ኑሮ ቅንጦት ነው፤ ባለንብረት ለመሆን መሞከርም የትግሬ ጠላት ማፍራት ነው – ስንትና ስንት አማሮች  በመርዝና በሰው እጅ በሥውርና በግልጽ እንደተገደሉ ለቀጣዩ ዘመን አድርሶን ከታሪክ ማኅደር ስናነብ እንደአዲስ ልቅሶ የምንቀመጥበት ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ብዙ ማለት በተቻለ – አነሳሴ ለዚያ አይደለም እንጂ፡፡ ለዚህም ነው አዲስ አበባ በሕዝባዊ ዐመፅ ቀዝቃዛ የሆነችው ማለት እንችላለን – ለአራት አማራና ኦሮሞ አንድ ወያኔ ሰላይ ይመደብላቸዋል፡፡ መፈናፈን የለም፡፡ ይህ ሁኔታ በራሱ ወደፊት የሚያስከትለውን መዘዝ ስናስበው ከአርማጌዴዮን የማይተናነስ ፍጅት እንደሚያስከትል ጥርጥር የለውም፡፡ ቀኑ ሲደርስና ፊሽካው ሲነፋ  እዚሁ መተላለቅ ነው፡፡ ክፉን በሩቅ ያድርግልን እንጂ ጥቂቶቻችን በሦስተኛው ዐይናችን እያየን ያለነው  የመከራ ዶፍ ብዙ የመኸር ወቅት እንደሚጠይቅና ብዙዎችን እርትም እንደሚያደርግ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ወያኔዎች ከመነሻቸው ጀምሮ በተለይ በአማራና ለአማራ ራሮት ባለው ወገን ላይ ሁሉ – በለዘብተኛ ትግሬም ላይ ሳይቀር – የፈጸሙትን ግፍና በደል ላስተዋለ መጪው ዘመን ለወያኔ ምን ይዞ እንደሚመጣ ለመተንበይ ሁሴን ጅብሪልን ወይም ኖስትራዳመስን መሆን አይጠይቅም – ጡት ያልጣለ ሕጻንም በግልጽ ይታየዋል፡፡ (መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ!” ይል ነበር፡፡ ጤናማ ትግሬዎች ወንድሞቻችንን ምከሩ – ጊዜ ካላቸው!)

ስለዚህ እባካችሁ ሌት ከቀን እንጸልይ፡፡ እዚህ በሀገር ቤት ቤተ ክህነቱም ቤተ እስልምናውም በወያኔ ስለተያዘ ከዘወትር ጸሎት ውጭ የተለዬ ምህላና እግዚኦታ መያዝ አይፈቀድም፡፡ ቤተ ክህነቱን በተለይ ከአቡነ ዘበሰማያት ያለፈ ዕውቀት የሌላቸው ወያኔ  ጳጳሣትና ቀሳውስት እንደተምችና አንበጣ ወርረው ይዘውታል፤ ደህና ካህናት ቢኖሩ እንኳን የሚናገሩትንና የሚሰብኩትን ከእግር እግር እየተከታተሉ የሰላምና የዕርቅ ነገር እንዳያነሱ በጥብቅ ያስጠነቅቋቸዋል፤ ሲፈልጉ ከሥራ አባርረው ለማኝ ያደርጓቸዋል፤ ከዚህም ባለፈ ለእስርና ለግድያም ይዳርጓቸዋል – ሰይጣን በአካል ተከስቶ ቤተ ክርስቲያንን እያስተዳደረ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የፊጥኝ ነው የታሰርነው ወገኖቼ፡፡ የዛሬ ወመኔ ቄስና ጳጳስ  አለባበሳቸውን ከማሳመር ባለፈ እንኳንስ “ግብረ ድንግል”ንና “የዐቢ ክብራን” “በስማም”ንና “ነአኩተከ”ን እንኳን በቅጡ አይዘልቁም፡፡ ወያኔ ከጅማሮው ኦርቶዶክስንና ያንን የፈረደበትን ሕዝብ  ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እንደመነሳቱ ምኞትና ህልሙ ተሳክቶለት ዛሬ ኦርቶዶክስም ሞታለች፤ አማራውም አብዛኛው የተሰናዳለትን የጥፋት ድግስ ባለመረዳቱ አልነቃም – እያንጎላጀ እንደተኛ አለ፤ ዐውቆ የተኛን መቀስቀስ ደግሞ  አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን አድካሚም ነው፡፡ ከነቃና ለመብቱ ከተነሳ ግን ጉንዳንም ሱሪን ታስወልቃለችና እነዚህ ወያኔዎች መግቢያ የሚኖራቸው አይመስለኝም –  የማይቀርን ነገር ማስታወሴ እንጂ ወያኔን ለማስፈራራት መሞከሬ አይደለም፤ ግዑዝ አይፈራም፤ ኅሊናው በጥጋብ ሞራ የተጋረደበትም እንዲሁ፡፡ የትግራይ ሕዝብ ግን ከወንድሞቹ ከአማሮች ጋር ያለውን ታሪካዊ ትስስር ማጥበቅና  ነግ በኔን መገንዘብ ይኖርበታል – ዛሬ ትናንትን እንዳልሆነ ሁሉ ነገንም በዛሬነት መጠበቅ የዋህነት ነው – ሁሌ ፋሲካ የለም ጋሽዬ፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ይህ የሎሚ ተራ ተራ ነገር ሰው ሰራሽ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ነውና ዛሬን ከትናንትናና ከነገ ጋር በማነጻጸር ሁሉም ቀልብ መግዛት ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ትምክህትም እንበለው ትዕቢትና ዕብሪት ማንንም ለዘለቄታው አይጠቅምም፡፡ ከልብ መሆንና ማስተዋል ግን ዘላለማዊ የሆነ የማያስወቅስ ስብዕናን ያላብሳል፡፡ የተገኘን ዕድል በጥበብ መጠቀም በታሪክ ያስወድሳል፤ በተቃራኒው ደግሞ የተገኘን ዕድል አልባሌ ማባከን በታሪክ ማኅደር ሊለቅ የማይችል ጥላሸትን ይቀባል፡፡ ለዛሬ ጥቅምና ፍላጎት ብለን ነገን መግደል የራስን ትውልድም እንደመግደል ይቆጠራል፡፡ ልጆቻችን አንገታቸውን ደፍተው እንዲሄዱ ሳይሆን ኮራ ብለው እንዲራመዱ የማያሣፍር ታሪክ ልንተውላቸው ይገባናል፡፡ ምርጫውን ለልባሞች ልስጥና በ“ቻው” ልሰናበት፡፡ ቸር ያሰማን፤ መልካም ክራሞት፡፡ የሰሞኑን የአምቦን ጨምሮ በየቦታው ወያኔ የሚጨፈጭፋቸውን ልጆቻችንን ነፍስ ይማር፡፡     [email protected] ትግሬ

Leave a Reply